Tex AARA2

Tex AARA2


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ግዢው መለያ ቁጥር ፡- አስከመባ/ መደበኛ/ ቡ1/003-02/2012

የተለያዩ ዓይነት የተዘጋጁ ደንብ ልብሶች ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ ደንብ ልብሶች፣ የአደጋ መከላከያ ጫማዎች እና የአደጋ መከላከያ የደህንነት ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል ።

ስለዚህ ፡-

ተጫራቾች በዘርፉ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ መመዝገብ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የተለያዩ ዓይነት የተዘጋጁ ደንብ ልብሶች ፣የተለያዩ የአደጋ መከላከያ ጫማዎች እና የተለያዩ የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች በጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 2 ክፍል 6 ላይ ዝርዝር ላይ ስሚቀርበው መሠረት ይሆናል ::

ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 2 ክፍል 6 ፍላጎቶች ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን ዕቃዎች ናሙና ከጨረታው መክፈቻ እለት በፊት እስከ ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው የባለሥልጣኑ መ/ቤት ዕቃ ግ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ መክፈቻ ዕለት የሚቀርቡ ናሙናዎች በባለሥልጣን መ/ ቤቱ ተቀባይነት ስለማይኖረው የጨረታ ሰነዳቸው ሳይከፈት ለተጫራቹ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ የሚቀርበው ናሙና ከእያንዳንዱ በጥንድ ለሚቀርቡ በጥንድ አንድ ሌሎች ዕቃዎች በቁጥር ለሚቀርቡ በቁጥር አንድ አንድ እንዲሁም በሜትር ለሚቀርቡ ናሙና ጨርቆች ስፋት መጠን 1ሜ በ1 ሜ መሆን አለበት፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈ ል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም በባንክ ሰተረጋገጠ የክፍያማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ተጫራቶች ባቀረቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሠንጠረዥ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ እማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሁሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡-011-3-72-15-28/011-3-71-41-03/011-3-72-00-47

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 16, 2020


© walia tender

Report Page