#TPLF

#TPLF


ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ። ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።

ህወሐት በመግለጫው በአሁኑ ጊዜ ኃገሪቷን ሊበታትን ያለው ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበ የትምክህተኞች ቡድን ነው፤ ይህ ኃይል እንደፈለገ እንዲንቀሳቀስ እድል የሰጠው ደግሞ አዴፓ ስለሆነ አዴፓ በአጠቃላይ ስለ ጥፋቱ፤ በፓርቲው አመራር ላይ የተፈፀመውን ግድያ በዝርዝር ገምግሞ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንዲሁም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ብሏል።

ሲቀጥልም በጄኔራሎቹና በአመራሮቹ ላይ የተፈፀመው ግድያ በሃሳብና በተግባር በቀጥታና በተዘዋዋሪ እጅጃቸው ያለ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ገለልተኛ በሆነ አካል በአስቸኳይ ሊመረመር ይገባል፤ ውጤቱም ለህዝብ በየጊዜው በግልፅ መነገር አለበት ሲል ያሳስባል።

የተቋሞች ሃላፊዎችና የፀጥታ ተቋማት መሪዎች ተገቢውን ኃላፊነታቸው ባለመፈፀማቸው ለተፈጠረው ጥፋት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ይላልም መግለጫው።

ውስጣዊ ችግሮቹን ከመገምገም ይልቅ በነገሩ የሶስተኛ አካል እጅ አለበት በማለት ጥፋቱን ለመሸፋፈን መሞከርና ህዝቡን ማደናገር ማቆም አለበት ሲልም ህወሐት አዴፓን ይወነጅላል።

ስለዚህ አዴፓ ውስጣዊ ችግሮቹን ፈትሾ አቋሙን እንዲያሳውቅም እንጠይቃለን፤ ይህንን ማድረግ ካልተቻለ ግን ህወሃት ከፓርቲው ጋር ለመስራትና ለመታገል እንደሚቸገርም በመግለጫው በግልፅ አስቀምጧል።

እስካሁን ያጋጠሙ መሰረታዊ ችግሮች በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የአሰላለፍ መደበላለቅና ኢህአዴግ ሁሉንም አይነት ጥገኛ አመለካከቶች ተሸክሞ የሚኖር ድርጅት እየሆነ ስለመጣ ነው። ቀድሞ ወደሚታወቅበት ባህል ተመልሶ በህግና በደንቡ መመራት ይገባዋል።

ኢህአዴግ እንደ ግንባር ሆነ እንደ መንግስት በቀጣዩ ዓመት መደረግ ስላለበት ሀገራዊ ምርጫ ያለውን ቁርጥ ያለ አቋም እንዲያሳውቅ በመግለጫው ተይቋል።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እየተነሱ ያሉት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ ከዚህ ዉጪ የህዝብ ጥያቄ በሀይል ወይም በሌላ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲልም ያስረግጣል መግለጫው።

Via #BBC

Report Page