#TIKVAH

#TIKVAH


ዛሬ ታህሳስ 13/2012 ዓ/ም ነው፤ የመጀመሪያው የዓመቱ የትምህርት አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ናቸው የሚቀሩት!


ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣት ተማሪዎቻችን ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለማጣራት ዛሬ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ ውሏል። አሁንም ችግሮች ያልተቀረፉበት ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ለመረዳት ችለናል። 


5 ዓመት ሙሉ የለፉ ተማሪዎች ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው ከወጡ፤ ከጓደኞቻቸው ተነጥለው ከትምህርት ገበታቸው ከራቁ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል። አዲስ ገቢ ተማሪዎችም በመጀመሪያ አመት ባዩት ነገር፣ በገጠማቸው ችግር፣ ባደረባቸው ፍራቻ ምክንያት ቤታቸው ከገቡ ቆይተዋል። ዛሬም የማስፈራሪያ መልዕክቶችን የሚሰራጩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ታዝበናል። የፌዴራል ፖሊስ ተመድቦ ለውጥ የመጣበት ግቢ እንዳለ ሁሉ ስጋቶች ያልተቀረፈበት ግቢም አለ።


ትላንት፣ ዛሬ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተማሪዎች የሚማሩበትን ተቋም ጥለው ወደቤተሰቦቻቸው ለመሄድ የወጡም አሉ። በስጋት ምክንያት የሚወዱትን ትምህርት ጥለው የወጡ ተማሪዎች ባሉበት ትምህርት የቀጠሉ ተቋማትም አሉ። አንዳንድ ተቋማት ተማሪዎች እንዲመለሱ ጥሪ ከማቅረብ የዘለለ መሬት ላይ የሚታይ ያለውን ስጋት ሙሉ በሙሉ የሚቀፍ ተማሪን ከተማሪ የማግባባት ስራ እየሰሩ እንዳልሆነ መልእክታቸውን የላኩ ተማሪዎች ገልፀዋል።


መንግስት ችላ ብሎናል፣ ውይይቶች፣ ምክክሮች እየተደረጉ ነው የኛ ችግሮች ግን እየተፈቱ አይደለም ያሉም በርካታ ናቸው። ውድ የሆነው የትምህርት ጊዚያችን እየባከነነው መፍትሄ ይሰጥን ሲሉ ተማሪዎች ጠይቀዋል።


ያነጋገርናቸው መምህራን ደግሞ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች በግቢያቸው ምን እየተፈጠረ እንዳለ፣ ትምህርት በምን አይነት ሁኔታ እየተሰጠ በደንብ ያውቃሉ ነገር ግን ችግሮችን እያዩ ዝም ብለዋል ሲሉ ገልፀውልናል። መግስት የት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደወጣ ያውቃል፤ እጅግ ለሀገር አደጋ በሆነ መልኩ በርካታ ተማሪ አንተ ከዚህ ስለመጣህ መማር አትችልም ተብሎ ለቆ እንደሄደም ያውቃል ይህን ችግር በፍጥነት ካልተፈታ በሰላም የሚማሩ የሌሎች ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የስነ ልቦና ጫና ማድረሱ አይቀርምና ይታሰብበት ብለዋል።


ችግር ተፈጥሮባቸው በማህበረሰቡ፣ በዩኒቨርሲቲው ጥረት፣ ወደ ሰላም የተመለሱና አሁንም እጅግ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ላይ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችም አሉ። ስለምን እነዚህ ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መፍትሄ ማምጣት አልተቻለም?? አሁንም የሀገራችን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ችግር ይፈታ እንላለን። አንድም ተማሪ ቢሆን በመንግስት ስንፍና ከትምህርት ገበታው ርቆ ቤቱ መቀመጥ የለበትም።


የህግ የበላይነት ይከበር!


መልዕክቱ ለሚመለከታችሁ አካላት!


የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች በ @tikvahethmagazien

Report Page