TIKVAH
ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ...
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሞጣ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አመሻሽ ላይ (ከ1:30) ጀምሮ በከተማዋ በሚገኘው የታላቁ ጀሚዑል ኸይራት መስጂድና ሌሎች ሁለት መስጅዶች ላይ የማቃጠል ተግባር መፈፀሙ ታውቋል።
ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በጥንታዊው የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ቃጠሎ መድረሱን ተከትሎ እየደረሰ ያለው ይህ መስጂዶችን የማቃጠል አጥፊ አካሄድ እጅግ በጣም አስደንጋጭም አሳዛኝም ነው። በከተማዋ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም ከአካባቢው መረጃዎች ደርሰውኛል።
የሱቆች ዝርፊያም እየተካሄደ እንደሆነና በሰዎችም ላይ አደጋ ደርሷል እየተባልኩ ነው። የሁለቱ እምነት ተከታዮች በከተማዋ ለእልፍ አመታት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንደሚኖሩ እየታወቀ በዚህ መልኩ መስጂዶችን መድፈርና ነዋሪዎች ግጭት ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ የሚደረገው ሁኔታ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል።
የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሁኔታው ከዚህ የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት ሊያስቆሙትና ለደረሰው ውድመት ተገቢውን ካሳ በመክፈል አጥፊዎችንም በመለየት ለህግ ሊያቀርቡ ይገባል።
(ኡስታዝ አቡበከር አህመድ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia