#TIKVAH

#TIKVAH


- ባለፈው አንድ አመት ተኩል ትልቅ ነገሮች ባይሰራም እንደ አንድ የለውጡ መነሻ ጥሩ ጅማሬ እንደሆነ ተናግረዋል።

- በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ላለፉት 80 ዓመታት የተለያዩ ኢትዮጵያ ላይ በነበሩ ስርዓቶች ተደጋጋሚ ጦርነትና ግጭት ሲፈጠር እንደነበር ጠቅሰው መነሻው ምንድነው በሚለው ላይ ደግሞ የውጭ ኃይሎች በአካባቢው ሰላም እንዳይኖር፣ ሁለቱ ሀገሮች ተስማምተው እንዳይኖሩ እንቅፋት በመፍጠር ከተለያዩ ስርዓቶች ጋር ስምምነት በማድረግ ጉዳዩን እዚህ ደረጃ ላይ አድርሰውታል ብለዋል።

- ላለፉት 20 ዓመታት በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው የድንበር ግጭት ዋነኛ መነሻው ከውጭ ኃይሎችና በ20 ዓመቱ ወቅት ስልጣን ላይ የነበረው በህወሓት የተፈጠረ ችግር ነው።

- በዓመት ተኩል ውስጥ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት ለመቀልበስ አሁንም በየጊዜው የተለያዩ ችግሮች እየተፈጠሩ የተለያዩ አዳዲስ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ግንኙነቱን ለማደናቀፍ እየተሞከረ ነው የጠቀሱት። 

- በፕሬዘዳንቱ አገላለፅ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን ይመራ የነበረው የህወሓት መንግስት አሁንም ድረስ ዶ/ር አብይ ስልጣን ከተረከቡበት ሰዓት ጀምረው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ድንበሩ እንደሚሰመርና ሰላምም መተግበር እንዳለበት ቃል ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የህወሓት ድርጅት ይህንን ለማደናቀፍ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያና በኤርትራ የተጀመረውን ሰላም ወደ ሌላ ደረጃ እንዳይቀጥል እንደትልቅ እንቅፋት እንደሆነ ነው የገለፁት።

- ባድመ አከባቢ ህወሓት መንግስት ለአዳዲስ ሰዎች ለእርሻና ለቤት መስሪያ እየሰጠ ድንበሩ እንዳይሰመር ትልቅ እንቅፋት እየፈጠሩ እንደሆነና በአሁን ሰዓት ደግሞ በህወሓት መሪዎች እየተነገረ ያለው በኤርትራ ኢሳያስ እና በኢትዮጵያ አብይ ስርዓት ተከበናል ለመጨፍለቅ እየተሰራ ነው የሚል አዲስ ስልት ይዘው እየሄዱ እንደሆነ ገልፀዋል። በሁለቱ ሀገሮች የተጀመረውን የሰላም ለማደናቀፍም በኢትዮጵያም የብሄርና የሃይማኖት ግጭት እና የተለያዩ ችግሮችን ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል። በዚህም ስምምነቱ ወደተፈለገው ደረጃ እንዳይደርስ እንቅፋት ለመሆን የህወሓት መሪዎች እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል።

Report Page