Stat 1

የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወ/06 የሚገኘው የፊታውራሪ ላቀ አድገህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
የጽዳት ዕቃዎች፣
ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ አካላት
በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000 ( አምስት ሺህ ) በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ዓይነት ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በነጠላና በጥቅል ዋጋ በመሙላት የግዢውን ዓይነት በኤንቨሎፑ ላይ በመጥቀስ እና ማህተም በዋናውና በኮፒው ላይ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛ ቀን ከቀኑ 11 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በት/ ቤቱ ይከፈታል፡፡
የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ በማሸግ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም፡፡
ት/ቤቱ የሚጫረተውን ዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ የሚችል ሲሆን ተጫራቶች ላሸነፉት ዕቃ የ6 (ስድስት) ወር ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡
ት/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አሸናፊው ድርጅት ማለፉን ካረጋገጠ በኋላ ያለፈበትን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በት/ቤቱ ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
አድራሻ :ቄራ ፊታውራሪ ላቀ አድገህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሶፊያ ሞል ጀርባ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0114-70-41-67 ወይም 0114-1672-65 ወይም 0114 66 98 32 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ት/ ጽ/ ቤት የፊታውራሪ ላቀ አድገህ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤት
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን አርብ መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline :2020-03-29