St s1

የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ በአራዳ ክ/ከ/ወረዳ የቤት ቁጥር ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች፡-
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ያለው ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ከሊራንስ ማምጣት የሚችል፣የአቅራቢነት የምስክር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
በስራ ዘርፉ ከሁለት አመት በላይ የስራ ልምድ ያለው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገዝታችሁ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በተቋሙ ዋ/መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 211 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከ2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው በ11 ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መከፈቻ ቦታ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና መ/ ቤት 2 ኛ ፎቅ አዳራሽ ቁጥር 207 ነው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይንም ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ምልክት ያልተደረገበት፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ እና የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ያሰርዛል፡፡
አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
ከገዙት /ከወሰዱት ሰነድ ውጭ ሞልቶ መመለስ ከጨረታ ያሰርዛል፡፡
የጨረታው ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገጿል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
አድራሻ፡- ችርችልጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር ፡-011 1 11 1512/011 1262246
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ ማ
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Equipment/Appliances, Purchase.
Posted Date :አዲስ ዘመን መጋቢት 24 ፥2012
Deadline :2020-04-16