St 56

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች
ሎት አንድ የጽህፈት መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።
የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ።
ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሳለሚያ ወረዳ 04 ወጣቶች ማዕከል ፊት ለፊት የእህል በረንዳ አካባቢ ገበያ ልማት የሱቆች ግንባታ አክሲዮን ማህበር ህንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 06 ግዥና ፋይናንስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (ኣስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓ. ም. ከሰዓት 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ሚያዝያ19 ቀን 2012 ዓ. ም. ከሰዓት 8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-27-89- 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
አድራሻ፡- መሳለሚያ ወረዳ 04 ወጣቶች ማዕከል ፊት ለፊት የእህል በረንዳ አካባቢ ገበያ ልማት የሱቆች ግንባታ አክሲዮን ማህበር ህንጻ ላይ 3 ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ ጽ/ ቤት
_______________________________
Category : Office Supplies and Stationery, Stationery Supplies, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን ሚያዝያ 5 ቀን 2012
Deadline :2020-04-27