Soft 1

Soft 1


stay home stay safe

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር MTO/NE-04/2012

በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በተለያዩ ሎት የተከፋፈለ ግዥ ማከናወን ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ፡፡
ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተጠቀሰው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ በተመሠከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ካዛንችስ የሚገኘው አሉ አዲስ ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6-5 የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡ 30 በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0115-57-77-93

የመካከለኛ ግብር የመ/ ከፋዮች ቅ/ ፅ/ ቤት


Posted:አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20 ቀን 2012
Deadline: May 12, 2020


©walia tender



Report Page