Sheger FM

Sheger FM

Sheger FM 102.

"... የፌዴራል መንግስት በልዩ ሁኔታ ካለው መጠባበቂያ በጀት ላይ ክልሉን እንዲያግዝ ጠይቀናል" - ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ

የአማራ ክልል መንግስት ከፍተኛ የበጀት ጫና ውስጥ እንደሚገኝ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው ለሸገር ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

ፌዴራል መንግስት ለክልሉ በሚደለድለው በጀት ውዝግብ ውስጥ እንደነበረ ያሳታወሰው ቢሮው በክልሉ ያጋጠመው ወቅታዊ ሁኔታ ተጨምሮ ችግሩ መበርታቱን ገልጿል።

የእንደ አማራ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ መረጃ ዘንድሮ በጀት ሰማንያ ቢሊዬን አንድ መቶ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺ ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ነው።

የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በበጀት ዙሪያ ያለውን ቅሬታ እንደሚከተለው አብራርተዋል ፦

" መጀመሪያ በ1999 ዓ/ም የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ተደርጎ መረጃ ሲወጣ ብዙ ክርክር የተደረገበት፣ ውዝግብም የነበረበት እንደሆነ ይታወቃል። 

በወቅቱ የአማራ ህዝብ አመታዊ የእድገት ምጣኔ 1.7 ፐርሰንት ተብሎ ነበር የተሰላው፤ ይህም ከሁሉም የሀገሪቱ ክልል #የመጨረሻው ነው።

ይህ ግን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲተያይ ብዙ አሳማኝ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉ ያመላክታል።

የአማራ ክልል ህዝብ ከሌላው ክልል ህዝብ የተለየ ባህሪ የለውም፤ የተለየ የእድገት ምጣኔ ሊኖረው የሚችልበት አሳማኝ ምክንያት የለውም። 

ይሄ እንደገና መታየት አለበት በትክክል አልተሰራም ፣ ስህተቶች አሉ የሚል ቅሬታ ነበር በወቅቱ ፤ ይህን መሰረት ተደርጎ ኢንተርሴንሳል ሳምፕሊንግ መንገድ ተጠቅመው እንደገና የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ይደረጋል በየክልሎቹ 2004 ዓ/ም 2005 ዓ/ም ይመስኛል ድጋሚ ቆጠራ ተደርጎ ሳምፕል ተወስዶ የእድገት ምጣኔው ወደ 2.34 ፐርሰንት አድጓል በሚል ማሻሻያ ተደርጎ ቀርቧል።

በዛ ፐርሰንት ካደገ ከታች ጀምሮ 1999 ፣ 1998 የነበረው ቤዙ በዛ ደረጃ ቢያንስ ሙሉ ይቆጠር የሚለውን ትተትን በዛ ብቻ መስተካከል ነበረበት ያ ስላልተስተካከለ አጠቃላይ ክልሉ ለበጀት ክፍፍል ታሳቢ የሚደረግበት የህዝብ ቁጥር እንዲያንስ ተደርጓል ፤ ብዙ የበጀት ማከፋፈያ ቀመሩ ላይ የተካተቱት ብዙ ፓራሜትሮች ደግሞ የህዝብ ቁጥርን መሰረት ያደረጉ ናቸው "

ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ የህዝብ ቆጠራ ካልተደረገ ወይም ደግሞ ፖለቲካዊ ውሳኔ ካልተሰጠ በስተቀር ቀመሩን ለመቀየር ሁኔታው አይፈቅድም ያሉ ሲሆን ነገር ግን በፌዴራል መንግስት ልዩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው የበጀት ጉዳዮች አሉ ብለዋል። 

ይህንንም እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል ፦

" ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ክልላችን አንደኛ አጠቃላይ የገቢው ሁኔታውን ጎድቶታል።

የንግድ፣ የግብርና፣ የቱሪስት ፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በሙሉ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። ስለዚህ ከዚህ ይገኝ የነበረው ገቢ በሙሉ ማግኘት አይቻልም በዚህ በጀት ዓመት።

በተለይ ሁለቱ ዞኖች ሙሉ በሙሉ በጠላት ቁጥጥር ስር ናቸው፤ ሶስት ዞኖች ደ/ወሎ፣ ደ/ጎንደር፣ እና ሰ/ጎንደር በከፊል የተወሰነው ክፍላቸው አሁንም በጦርነቱ ሰለባ ስለነበሩ እንቅስቃሴያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል። እነዚህን ወደነበሩበት ለመመለስ ከፍተኛ ሀብት ይጠይቃል ይሄንን የፌዴራል መንግስት በልዩ ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገብቶ ካለው መጠባበቂያ በጀት ላይ ክልሉን እንዲያግዝ እንጠይቃለን።

ባለፈው ከጥቅምት 24 ጀምሮ በነበረው ጦርነት የነበረውን ጉዳት እና ክልሉ እያወጣ የነበረውን ወጪ ግምት ውስጥ አስገብተን የሪከቨሪ ፕላኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የፌዴራል መንግስቱ የበጀት እገዛ እንዳያደርግልን ጠይቀናል"  

ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ወደ ክልሉ የተቀላቀሉ 18 ከተሞች እና ወረዳዎች እንዲሁም የአንድ ዞን ሰራተኞች ደሞዛቸውን እና ሌሎች ወጪዎቻቸውን እየተሸፈነ የሚገኘው በክልሉ መሆኑን ዶ/ር ጥላሁን ተናግረዋል።

ክልሉ ያለበትን ጫና በተመለከተ ለፌዴራሉ መንግስት ጥያቄ ቀርቦ ውሳኔውን በትስፋ እየተጠባበቅን ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ምንጭ ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopia

Report Page