Sft vic tx maint

Sft vic tx maint


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 04/2012

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የቅ/ጽ/ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት

የሠራተኞች የሰርቪስ መኪና ኪራይ፣
የተሽከርካሪ ጥገና የጋራዥ አገልግሎት፣
የሰራተኛ ስራ ልብስ ጨርቅ፣
የአደጋ መከላከያ፣
የጤና መጠበቂያ እና ጫማ፣
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
የጽዳት ዕቃዎች፣
የሞተር ሳይክል ጎማ ግዢ፣
ልዩ ልዩ መሳሪዎች፣
ቋሚ ዕቃዎች ማሽነሪዎች/፣
ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/፣
ምንጣፍ፣
የጀነሬተር ጥገና እና
ለቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮዎች የኔትወርክ ዝርጋታ
የእጅና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ዋጋ ጨምሮ፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ተጫራቾች፡-

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የአቅራቢነት ዝርዝር በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት ወረቀት (በቅርብ ጊዜ ፕሪንት የተደረገ)፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር ከሚከፍልበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታውን ሰነድ የማይ መለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ኖክ ማደያ አዲሱ ህንፃ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስ ትና ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ/BID BOND/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃና አገልግሎት ግዢዎች በመሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የተሽከርካሪ ጥገና (የጋራዥ) አገልግሎት ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የሰርቪስ መኪና ኪራይ አገልግሎት በሰነዱ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሰረት በቀን የሚከፈል ቁርጥ ዋጋ ማቅረብ እንዳለበትና ተወዳዳሪው ድርጅት በአዲስ አበባ ውስጥ ተዘዋውሮ መስራት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
ለሚወዳደሩባቸው የጫማ፣ የአደጋ መከላከያ፣ የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በተመለከተ ከእየ አይነቱ አንድ አንድ ናሙና የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው የናሙናዎቹን ዝርዝር በሁለት ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከሚከፈትበት ሰዓት አስቀድሞ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ንብረት ሠራተኛአስፈርመው ማስረከብና አንዱን ኮፒ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ሙሉ አድራሻቸውና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4 ፡00 ሰዓት የጨረታሳጥኑ ታሽጎ በ45 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን በጽሑፍ ለቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በ5 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች ቡ5 ቀናት ውስጥ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቀርበው ግዢውን ከሚፈፅመው አካል ጋር ውል ይፈፅማሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118-88-54-95/0114-40-37-66 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ

በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አዲሱ ህንፃ 5 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ግዢና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ

ቅ/ ጽ/ ቤት



_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Energy, Generators, Furnishing and Fixture, Carpets and Curtains, Furnitures, Office Furniture, Machinery., Purchase., Rent., Security and Protection, Security and Protection Equipment, Software/ Website and Networking, Network Installation and Troubleshooting, Networking Tools and Accessories, Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing, Leather Products, Vehicle and Spare Parts, Vehicle Rent, Vehicle and Motorcycle Maintenance, Tyre and Battery

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 25፥2012
Deadline :2020-04-18

Report Page