Sell con mach eep

Sell con mach eep


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/01/2012

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ለተለያየ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የጽዳት አገልግሎት፣ የአትክልተኛ አገልግሎት እንዲሁም የክሬን እና ሎቤድ ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በሁሉም ሎቶች ወይም በከፊል ሎት መወዳደር ይችላሉ፡፡

-ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

-ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀን እና ሰዓት አዲሱ ኬኬር ሕንፃ ሜክስኮ አደባባይ ቄራ መንገድ በሚገኘው ዋና መ/ቤት አንደኛ ፎቅ ለሁሉም ሎቶች የማይመለስ ብር 300.00 ( ሦስት መቶ ብር ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

-ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የጽዳት አገልግሎት፣ የአትክልተኛ አገልግሎት እንዲሁም የክሬን እና ሎቤድ ኪራይ አገልግሎት ዋጋ ዝርዝር እና ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TSO/NCB/01/2012 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

-ተጫራቾች ሙሉ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ ደግሞ በስልክ ቁጥር፡- 011-5-58 19 16/011-5 58 17 25 መደወል ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 17 ቀን 2012

Deadline: June 10, 2020


© walia tender

Report Page