Secu 11

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ፌቴሙ/ መ/ ጨ/2/2012
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ በ2012 ዓ/ም ከመንግስት በተገኘ መደበኛ በጀት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም የዩፒኤስ፤ ደንብ ልብስ ማስታወቂያ እንደዚሁም
የኤጄንሲው ድረ ገጽ/ዌብ ዴቨሎፕመንት/እና
የጽዳትና
ጥበቃ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ ፍላጎት ያላችሁ
በዘርፉ ዕቃና የአቅርቦት አገልግሎት ዝርዝር ላይ የተመዘገባችሁ እና የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ
የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት /VAT/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልፅ የመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውን ቴክኒካል 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒውን እንደዚሁም ፋይናንሽያል 1 ኦሪጅናል ና 2 ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በፌዴራል ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስለጠና ኤጀንሲ ላምበረት መናሃሪያ አጠገብ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 ቀርበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ 4 ፡00 ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5 ፡00 ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ/ እሁድ / በዓል ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ይከናወናል፡፡
ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% እንደሁኔታው ከዛም በላይ በማስያዝ ባሸነፉበት በ7ኛ ቀን ውስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ያስያዘው ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ጨረታው 2ኛ ለወጣው ወይም ይሰረዛል::
ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ከሚሸጠው ሰነድ ላይ የተጠቀሰ በመሆኑ ገዝተው ማየት ይችላሉ፡፡
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0118619764 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Purchase., Security and Protection, Guarding
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline :2020-04-03