Sale water work eng wag 1

Sale water work eng wag 1


የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 007/2012

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ብ/ሰብ አስተዳደር እበ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች በ2012 በመደበኛ በጀት

የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች በሎት ምድብ 1፤2. በአስ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በደቢና በለቃ የጤና ጣቢያ የደረጃ ማሳደግ ግንባታ የሚሠራ በጤና ሚኒስቴር በክልል ጤና ቢሮ እና በአበወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በጀት የሚሸፈን የግንባታ ጨረታ እንዲሁም በአበ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በሴሪያ ጤና ጣቢያ የጣራ ላይ ውሃ ማሰባሰብ ግንባታ ጨረታ በክልል ጤና ቢሮ በጀት የሚሸፈን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት እና ማሠራት ስለፈለግን ጨረታውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል። ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡

ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የሚወዳደሩ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
በጤና ሚኒስቴር በክልል ጤና ቢሮና በአበ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በደቢና በለቃ የጤና ጣቢያ የደረጃ ማሳደግ ግንባታ ጨረታ የሚሳተፍ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት። እንዲሁም አበ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት በሴሪያ ጤና ጣቢያ የጣራ ላይ ውሃ ማሰባሰብ ግንባታ ጨረታ በክልል ጤና ቢሮ በጀት የሚሸፈን ሲሆን በዚህ ጨረታ የሚሳተፍ ከደረጃ 10 ጀምሮ ነው። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበር ከሆኑ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው በደረጃ 9 እና 10 የግንባታ ሥራዎች በተሰጣቸው ፍቃድ ላይ ሆነው ሲወዳደሩ ብቻ ነው።
የጽሕፈት መሳሪያ ዕቃዎች ውድድሩ በሎት መሆኑና ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱት የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በፖስታ አሽጎ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የሚጫረቱት እስፔስፊኬሽን ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በራሱ እስፔስፊኬሽን የሞላ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
ጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ከሞሉት ቫቱን ጨምሮ ከጠቅላላ ዋጋው 1.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታለ። እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ በተወዳደሩት ሎት ፖስታ ላይ ተያይዞ መገኘት አለበት።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋሲቀመጥ ቫትን የሚያካትት መሆኑን መግለጽ አለበት።ቫት በትክክል ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተቆጥሮ ውድድር ይካሄዳል።
ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የቀረበው ዋጋ በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል። እንዲሁም የአበርገሌ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሙላት አለበት።
ተጫራቾች የሚወዳደሩት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር/ ሃምሳ ብር/ ብቻ አበርገሌ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በ16 ኛው ቀን በመንግሥት የሥራ ሰዓት በ2፡00 ሰዓት እስከ 2፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ገብቶ በ3 ፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም ከቀኑ በ4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአበ/ወ/ገ/ ኢ/ት/ጽ/ቤት በግዥ ቡድን ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ በሚቀጥለው የመንግሥት ሥራቀንና ሰዓት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቶች በራሳቸው ምርጫ ፍላጎት ባይገኙ የጨረታ መክፈቻ ቀን የማያስተጓጉል መሆኑን አውቆ ለተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው ውጤት ላይ ቅሬታ ካላቸው ለጽ/ቤቱ ማቅረብ ይችላሉ። በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ መስሚያ ቀናት በኋላ ባሉ በ5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውለታ መውሰድ ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች/ግንባታ ዋጋ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ እንደሚችል መረዳት አለባ ቸው። ነገር ግን በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተው ብዛት የተቋማት በጀት መሠረት አድርጎ ሊቀርብ የሚችል እንጂ የበጀት እጥረት ካለ ሁሉንም ማቅረብ እንደማይችሉ መረዳት አለባቸው።
አሸናፊ ድርጅት ባሸነፈባቸው ጠቅላላ ዋጋ 10% ለጽ/ቤቱ ውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል። የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚያስረክባቸው ዕቃዎች በራሱ ወጪ ትራንስፖርት እስከ በአበወ/-ኢ/ት/ጽ/ ቤት ሴክተር መ/ቤት በየንብረት ክፍል ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው። እንዲሁም ለግንባታ ጨረታ አሸናፊ 30% ቅድመ ክፍያ የሚጠይቅ ከሆነ 30% ማስያዝ አለበት።
ጨረታው በሎት ስለሆነ የሚወዳደሩት በጥቅል ዋጋ ነው። በመሆኑም በጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ያልተሟላ ካለ ውድቅ ይደረጋል።
ማንኛውም አሸናፊ ዕቃዎችን ርክክብ ሲፈጽም ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ የታሸጉ ዕቃዎችም ተፈተው ተፈትነው ተቆጥሮ እና ተለክተው ገቢ መሆን አለባቸው።
. የጨረታው ሳጥን ለመክፈትና ለማሸግ ዘግይተው የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም። የመጫረቻ ሰነድ ሞልተው ካቀረቡ በኋላ ትቼአለሁ ማለት አይቻልም።
. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የመወዳደሪያ ሃሳቡ በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ታሽጎ መቅረብ አለ በት።
በዚህ ያልተካተቱ ሕጎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/203 ተግባራዊ ይሆናል።
አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ፣ ጠቅላላ ዋጋ መሙላት፣ ቀን ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0924494178 እና 0949730306 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ብ/ ሰብ አስተዳደር አበ/ ወ/ ገ/ ኢ/ ት/ ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page