Sale vic tex buidessiecity admin1

Sale vic tex buidessiecity admin1


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 04/2012

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል

1ኛ በከተማው ውስጥ ለሚያሰራው የመንገድ ስራዎች ኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ የኦፕሬተር አበል ወጭ ፣ የነዳጅ ወጭ፣ የቅባትና ዘይት ወጭ ፣ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን አከራዩ ችሎ በሰዓት ተከራይቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
2ኛ. የተሽከርካሪ ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ ፣ የህንፃ መሳሪያ ሲሚንቶ ፣ ደንብ ልብስ ግዥ ፣ የቢሮ ቋሚ እቃ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስስዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾችበጨረታለመሳተፍከላይ ከተራቁጥር -3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ፣ የህንፃ መሳሪያ ሲሚንቶ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ የቢሮ ቋሚ እቃ አይነትና ዝርዝር ሙግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (በሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።

የመጫረቻ ሰነዱ የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን /አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን እናሳስባለን።

ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም ለኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ የማይመለስ ብር 100.00 በአንድ መቶ ብር/፣ለህንፃ መሳሪያ ሲሚንቶ የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/፣ ለሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/፣ ለቢሮ ቋሚ እቃ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/ አስ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/ የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል።

ጨረታው ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ይከፈታል የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዣ ማቅረብ ይኖርበታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም

በስልክ ቁጥር 033 31291-73/033311-1041/10-48/1059 በመደ ወል መረጃ ማግኘትይችላሉ።
አድራሻ፡ ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት ስፌት

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 12, 2020


© walia tender

Report Page