Sale vic buil 1

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን
የሞጆ ጉምሩክ ቅ / ጽ / ቤት .
የተተው ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ቁጥር 18/2012 የጨረታ መመሪያ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎችን በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 51 ንዑስ አንቀፅ 1 እና በእዋጅ 1160/2011 በአንቀጽ ቁጥር --- መሰረት በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ አስመጪዎች ዕቃቸውን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ፈጽመው ሳለመውሰዳቸው ምክንያት እንደተተው ተቆጥረዋል። ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 8 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም :-
የጽህፈት መሣሪያዎች ፣
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
ክሮች ፣
ፕላስቲክን የፕላስቲክ ውጤቶች ፣
ጎማዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፤
የፋብሪካ ግብዓት፣
የህንፃ መሣሪያዎችና ሌሎች ዕቃዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን።
ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ730-1፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 6፡00 የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ አሰባሰብ ቡድን መውሰድ ይችላሉ።፡
ተጫራቾች በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከባለሥልጣኑ የሚሰጥ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ሲያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተመሰረተለት CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እንደታወቀ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል። ተጫራቾች የሚያሲዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE 0946 ሲሆን የግል ባንከ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፎች፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግም በአዲስ አበባ፤ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለባቸው።
ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚገዙበት ዋጋ የሞሉበት ሰነድ፤ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 3፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣው መሰረት በ8 ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3 ፡45 ታሽጐ 4 ፡00 ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፉ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ያሸነፈበት ዕቃ ዋጋ በማድረግ እቃውን መረከብ አለበት። በአምስት ቀን ውስጥ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆና ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
በተራ ቁጥር ስድስት (6) በተቀመጠው ጊዜ ያሸነፈበትን የዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪው ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም እቃው በ2 ወር ውስጥ ካላወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይቻልም።
ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቶቆያል።
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም።
አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ይታገዳል። ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ሲሆን አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈው በህገወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታው ውጤት ይሰረዛል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ያቀረበውን ዕቃ ብዛት ሊጨምርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-01-90 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ
ኮሚሽን የሞጆ
ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 04 ቀን 2012
Deadline: May 21, 2020
© walia tender