Sale used comp amhara road 2

Sale used comp amhara road 2


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፀውን ቢትመን በርሜሎች መሸጥ እንዲሁም የተለያዩ ኮምፒውተሮችን እና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት ወይም ግለሰብ በባህር ዳር ከተማ ድርጅታችን ዋናው ቢሮ ድረስ በመምጣት የሚሸጡ ቢትመን በርሜሎች እና የዋናውን ቢሮ መዝናኛ ክበብ በአካል በማየትና የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች በድርጅታችን ስም ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ በተራ ቁጥር 2 ቢትመን በርሚል የጠቅላላ ዋጋቸውን 10 በመቶ እንዲሁም በተራ ቁጥር 1 እና 3 ለተገለፀው የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ ኮምፒውተሮችና ኤሌክትሮኒክስ ግን በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቶዮታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው ሆኖ ለእያንዳንዳቸው የጠቅላላ ዋጋቸውን 2 በመቶ ብር በማስያዝ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት ወይም ግለሰብ በሚመርጥበት ጊዜ የሚሸጠውን ቢትመን በርሚል/ሌሎች ግዥዎችን መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 50 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የሚሸጡ እቃዎች የሚያቀርቡበትን መግዣ ዋጋ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የሚሸጡ እቃዎች ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መ/ቤታችንና በድርጅታችን ባህር ዳር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም ፋይናንሻል ሰነድ አዘጋጅተው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ባህር ዳር ከተማ የሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊትየግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 9 ፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9 ፡30 ይከፈታል፡፡
በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 100 በመክፈል ከ ድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ውል ካልወሰደ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሣል፡፡ በተጨማሪም በተራ ቁጥር 2ለተገለፀው አሸናፊው ድርጅት ውል ከወሰደ በኋላ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እቃዎችን ሙሉ በሙሉ ማንሣት አለበት፡፡ በተባለው ቀን ካላነሰ መ/ቤቱ ለሌላ ድርጅት የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን አሸናፊውድርጅት እቃዎችን መርጦ መውሰድ ወይም መተው አይችልም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 3576 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት



Posted: በኩር ግንቦት 10ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page