Sale tex japan hidase14

Sale tex japan hidase14


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የኢትዮጃፓን ህዳሴ 2ኛደረጃ ት/ቤት የጨረታ ቁጥር 002/2012ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ለወጣው ለተለያዩ

የቢሮ እቃዎች፣ የቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
አላቂ የትምህርት እቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
አላቂ፤ የስፖርት መገልገያዎችና ትጥቆች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሠነዱን መግዛት የሚችሉት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡ ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ቲን ነምበር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሒሳብ የዕቃ ዓይነት ስም፣ የተመረተበት ሀገር፣ የሞዴል ቁጥር፣ የተመረተበት ጊዜ ያካተተ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ከዓይነቱ አንድ አንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ተሸናፊ ሲመልሱ የአሸናፊ ተጫራቾች ናሙና ዕቃው እስክ አቀረቡ ድረስ አይመለስም፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 60.00 / ስልሳ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኢ/ጃ /ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢን ንብረት አስተዳደር ደጋፊ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 3000.00 / ሶስት ሺህ / ብር በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር እና የዕቃውን ዓይነት በግልፅ ኢንቨሎፕ ላይ መፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኢ/ጃ/ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ኛው ቀን 10 ፡30 ሠዓት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ 11 ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢ/ጃ/ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
ተቋሙ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባስቀመጠው specification መሆናቸው ጥራት ዋስትና አጠቃሎ ማቅረብ ግምት ውስጥ ይገባል፡፡
ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ሌሎች ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
በስልክ ቁጥር፡-0114 34 68 43 / 2511188806 00 ፖስታ ሣጥን ቁጥር 540 ኮድ 1230

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ ያኢትዮ- ጃፓን ህዳሴ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: May 28, 2020


© walia tender

Report Page