Sale srtv24

Sale srtv24


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 003

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለቴሌቪዥን አውቶሚሽን ሲስተም የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡

በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመካተታቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች የሥራውን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከድርጅቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል የንግድ ፈቃድ ኮፒ በመያዝ መውሰድ ይችላሉ፡ ፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁለቱም የሚወዳደሩ ከሆነ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር / በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብቻ ከሆነ 5,000.00/አምስት ሺህ ብር/ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብቻ ከሆነ 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በ16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4 ፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-221-1351/046-220-4750/046 212-5541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መ/ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page