Sale sound1

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 03/2012 ዓ. ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በ2012 በጀት አመት ሳውንድ ሲስተም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በገ/ኢ/ል/ሚ/ር የእቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሊስት ዌብ ሳይት የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ፤የዘመኑን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾችን መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር / በመክፈል በብሔራዊ ቴአትር ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ሙሉ አድራሻቸውን ክ/ከ/ ወረዳ ፤ ቤት”ቁጥር ፤ስልክ ቁጥራቸውን በመጻፍ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን ከቀኑ በ 8 ፡ 00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር / ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) የጨረታ መክፈቻ ቀን ከመድረሱ በፊት ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 16 ኛው ቀን ከቀኑ በ 8 ፡ 30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል ትክክለኛው ቀን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የእቃው ርክክብ የሚፈጸመው በብሔራዊ ቴአትር ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ ከ ወረዳ 7
ለተጨማሪ ማስረጃ ፡- 0115513735 እና 0115158244 መጠየቅ ይቻላል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20 ፥2012
Deadline: May 13, 2020
© walia tender