Sale print omo kuraz 50

Sale print omo kuraz 50


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አግጨ /28/ አኩሰፋ 3/2012
በኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር 3 ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ

የጽህፈት መሳሪያዎች (Stationary Materials)፣
የተለያዩ የህትመት ስራዎች (Printing Materials) እና
የጽዳት እቃዎች (Cleaning Materials) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 5 በተገለፀው አድራሻ ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከሰዓት በፊት (ከሰኞ እስከ አርብከ2፡30-6፡00 ፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 ሰዓት እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ::
የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፣ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው:: አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ሜክሲኮ ከፌዴራል ፖሊስ ዝቅ ብሎ ከኢሲኤክስ ፊት ለፊት ፊሊፕስ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 405/409 ነው:: ስልክ ቁጥር :0920711749/ 0921501510/09450021106
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሠከረለት (CPO) (በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
ጥቅል ( ሎት) -1 የጽህፈት መሳሪያዎች (Stationary Materials) 10,000 ( አስር ሺ ብር)
ጥቅል ( ሎት) -2 የተለያዩ የህትመት ስራዎች (Printing Materials) 12,000( አስራ ሁለት ሺ ብር)
ሎት-3 የጽዳት እቃዎች (Cleaning Materials) 15,000 ( አስራ አምስት ሺ ብር)
የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈፀመው: አዲስ አበባ በሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር-3 ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ፡፡
ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የማቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ30 ቀናት ነው፡፡

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢ. ፌ. ዲ. ሪ ስኳር ኮርፖሬሽን የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር-3 ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 10 ቀን 2012

Deadline: June 27, 2020


© walia tender

Report Page