Sale other ozila

Sale other ozila


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር : AE-BID/001/20
አዚላ ኤሌክትሮኒክስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የፍሪጅ ካሳትን ወይም ፍሪጅ ለመገጣጠም የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከውጭ ለማስመጣት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቶች፡-

በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ኩባንያው የራሱ የሆነ የጥሬ እቃ አምራች ያለው በመሆኑ ተጫራቶች በአዚላ ኤሌክትሮኒክስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስም (For the Account of Azila Electronics PLC) 1920 የሚያስመጡ ሲሆን ጥሬ እቃዎቹ በአይነት በመጠንና በዋጋ የሚገለፁ ሲሆን ተጫራቾች በመንግስት በኩባንያው ወይም ሰአምራቶች የሰጠውን የታክስ ማበረታቻ (Tax Advantage) በመጠቀም ጥሬ እቃውን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ከጥሬ እቃ ዋጋ (FOB Price) ላይ የሚወዳደሩበትን የትርፍ ህዳግ (profit Margin) በፐርሰንት የሚያቀርቡ ሲሆን ከቅጣት በስተቀር ሌሎች የታክስ የማጓጓዣ፣ የኢንሹራስ እና ወዘተ ወጭዎችን አስመጪው በሚቀርበው አግባብነት ባላቸው ደረሰኞች መሰረት የሚወራረድ ወይም የሚተካ ሲሆን እነዚህ ወጪዎች የትርፍ ስሌት ተመን ውስጥ አይካተቱም ተጫራቾች ማንኛውንም አይነት የባንክ፣ የጉምሩክ እና የሎጂስቲክስ ፕሮሰሶችን ማስጨረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የትርፍ ህዳግ (Proft Margin) ህጋዊ የክፍያ ደረሰኝ ሲቀርብ በወቅቱ የምንዛሬ ዋጋ ተሰልቶ በኢትዮጵያ ብር የሚፈፀም ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250 ( ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር (ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት መንገድ) በሚገኘው አምባሰል ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተ ጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በሰላሳ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በሚገኘው አምባሰል ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607 ውስጥ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን ክብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው በግልፅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጨረታው ውጤት ለአሽናፊ እና ለተሽናፊዎች በእኩል ጊዜ በደብዳቤ ወይም በስልክ ወይም በድርጅቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ
ከፈለጉ +251913956794 ወይም +251930293761 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ:አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት መንገድ
አምባሰል ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 607
እዚላ ኤሌክትሮኒክስ

ኃ/ የተ/ የግል ማህበር



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 09 ቀን 2012
Deadline: May 26, 2020


© walia tender

Report Page