Sale other cat1

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2012
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል፡
ሎት 1 የፅዳት ዕቃዎች ግዢ
ሎት 2 የውሀ መስመር ጥገና አገልግሎት ግዢ
ሎት -3 ለሆስፒታሉ የምግብ ማደራጃ ክፍል የሚውሉ የምግብ አገልግሎት ግዢ
ሎት -4 የኤሌክትሪክ ምድጃ እና ፕሌት ግዢ
ሎት -5 የላውንደሪ ክፍል ማሽኖች ጥገና አገልግሎት ግዥ
ሎት -6 የሆስፒታሉን የካፌ አገልግሎት ግዥ
ሎት-7 የላውንደሪ ክፍል ማሽኖች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው፡
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚልፅ በግልፅ የሚታይ የፎቶ ኮፒ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ 150 ( አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ፣እሁድና የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10 ኛው ቀን 11 ፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ የፋይናንስ እና ክፍያ ዳይሬክቶሬት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማህተም ተደርጎ፣ በየሎቱ ለየብቻ በማሸግ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ በየሎቱ ለይቶ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ሰነድ ሲያቀርቡ፡- ፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በመለየት ታሽጎ መቅረብ አለበት ፣ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒው ለየብቻ በመለየት ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች ሳምፕል መታየት ባለባቸው ላይ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው ፡፡
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 የስራ ቀናት በኋላ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሎት-2 እና በሎት-5 ላይ የብር 1000.00 ( አንድ ሺ) በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሲፒኦ (CPO) በሆስፒታሉ ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፡- በሎት- 1 ፣ በሎት- 3 ፣ በሎት- 4 እና በሎት-6 ፣ በሎት-7 ላይ የብር 5000.00( አምስት ሺ) በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሲፒኦ (CPO) በሆስፒታሉ ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በተቀመጠው መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየትና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሀሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዥ ዳይሬክቶሬት በጽሁፍ ማቅረብ ወይም በስልክ መጠየቅ ይችላሉ
የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል፡፡
ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ከ7 ቀን በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ በሰባት ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በስፔስፊኬሽኑ እና በሳምፕሉ መሰረት ማቅረብ ያለባቸው እና የጥገና ስራዎችንም መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ለሚደርስ ሰነዱ ወደ ጨረታ ሳጥኑ ሳይገባ ተመዝግቦ ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል፡፡
ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የታጠቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር ፡-011-515 -02- 42 በመደወል መረዳት ይቻላል
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 ፍል ውሀ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል።
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 07 ቀን 2012
Deadline: May 25, 2020
© walia tender