Sale med lab kolfe w5

Sale med lab kolfe w5


የጨረታ ማስታወቂያ


በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ ስር የሚገኘው ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ለተለያዩ ክፍሎች ሥራ አገልግሎት የሚውል፡በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 05 ጤና ጣቢያ ለተለያዩ ክፍሎች ሥራ አገልግሎት የሚውል፡-

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 05 ጤና ጣቢያ

(ሎት 1 ) ቋሚ እቃ
( ሎት 2) አላቂ እቃ
(ሎት 3) መድሃኒት እና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች


በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 ለተጠቀሱት ግዥዎች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በእቃው አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ -ከ100,000 በላይ
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በሚገኘው ከተራቁጥር 1 የተጠቀሱትን ሥ ራዎች የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክ ፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላል።
ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋ ስትና ብር 3,000.00( ሦስት ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በመስሪያ ቤታችን (በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ስም) በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመግለጽ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን ዓይነት በመጥቀስ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት አለባቸው።

ጨረታው የሚከፈተው በ10 ኛው ቀን በ 11 ፡00 ሰዓት ሳጥኑ ተዘግቶ በ 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4.00 ሰዓት ተጫራቾ ች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሥራዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
አንዱ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

*መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሥራ በጤና ጣቢያው እንደ ትዕዛዙ ዓይነት ሥራዎቹን መሥራት ግዴታ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ ፡- ኮ/ ቀ/ ክ/ ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ(72 ሰባራ ድልድይ)

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0118114195


በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከ ስር የሚገኘው

ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 19 ቀን 2012
Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page