Sale hawassa water sewer6

Sale hawassa water sewer6


የጨረታ ማስታወቂያ

በድጋሚ የወጣ የኤሌክትሪክ መሣሪያ ዕቃዎች

የግዥ መለያ ቁጥር ግፋ/08/2012

የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በላይ በተገለፀው ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሠረት የሚፈለጉ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

- የ2012 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

- የተጨማሪ እሴት ታክስ ( የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣

2. የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 20,000 ( ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረ ጋገጠ ሲፒኦ ግዥውን በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከተጠየቀው ሲፒኦ ማስያዣ ውጪ ያቀረበ ጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

3. የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ/ን/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት ሠነድ ከልያዙ የጨረታ ዶክመንቱ አይሸጥም፣

5. የዕቃዎቹ ብዛት ተዘጋጅቶ በሚሸጠው የጨረታ ዶክመንት ላይ በዝርዝር ተገልጿል፣

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው

7.ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀም ሮ በ16 ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት እስከ 8 ፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ8 ፡30 ሰዓት ተ ጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡-046212 1580/ 046 22128826

ፖ. ሣ. ቁ፡- 108 አድራሻ ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር አስፋልት ፊት ለፊት

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 13, 2020


© walia tender

Report Page