Sale harari 1

Sale harari 1


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEU/PLW & F/NCB-003/2012

የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ቶነር ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ግንቦት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 በመምጣት የማይመለስ ብር ለሎት-1 ብር 400.00 ( አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ሐረር ራስ ሆቴል ጀርባ የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፕሮኩዩርመንት ሎጂስቲክስ ዌር ሃውሲንግ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 205፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ብር ለሎት 1 ብር 23,402.50 (ሃያ ሦስት ሺህ አራት መቶ ሁለት ብር ከሃምሣ ሣንቲም (50/00) በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEUPiw & F/NCB-003/2012 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ለሎት1- ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው ኣድራሻ ቢሮ ቁጥር 205 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሎት- ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 025-466-08 43 መደወል ይችላሉ፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት


Posted: አዲስ ዘመንግንቦት 12 ቀን 2012
Deadline: June 12, 2020


© walia tender

Report Page