Sale furn vic kirkos 18

Sale furn vic kirkos 18


በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 06/2012
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1ኛ. ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች።
2ኛ. ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎች
3ኛ. ሎት 3 የመኪና ጎማ
በመሆነም ተጫራቾች፡-

በዘርፉ ህጋዊና በ2012 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፡ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር/tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው።
ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
ለሚወዳደሩባቸው የእቃ አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች በመወዳደሪያ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን ዋጋ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የጨረታው ሰነድ አቀራረብ ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፡ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኦርጅናል በ አንድ ኤንቨሎፕ ያቀረበ ተወዳዳሪ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11 ኛው ቀን ላይ ከጥዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ 0115548264

በቂርቆስ ክ/ ከ/ አስ/ የዋና ስራ

አስፈፃሚ ፅ/ ቤት የግዥ ቡድን




Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 08 ቀን 2012

Deadline: May 26, 2020


© walia tender

Report Page