Sale furn begemider1

Sale furn begemider1


ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የበጌ ምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ስልክ ቁጥር 058 141 00 31 ለ2012 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የኮሌጃችን ተሽከርካሪዎችን 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሰርቪስ ለ1 ዓመት ውል እንዲያዝ ለማድረግ
የፈርኒቸር እቃዎች /ካዝና/
የጽዳት እቃዎች
ከዚህ ባላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ ዘዴ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ኮሌጁ ከብር 20000.00 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ግዥ ሲፈጽም መንግስት በሰጠው ውልክና መሰረት 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
ኮሌጁ ከብር 10 ሺህ በላይ ግዥ ሲፈጽም 2 በመቶ የዊዝሆልዲንግ ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ቁጥር ብዛት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ን የማይመለስ 30.00 በመክፈል ከግ/ ፋ/ ንብ/ አስ/ ደ/ የስራ ሂደት ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ወይም 9 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ተገልፆላቸው ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል መስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናውን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን 4 ፡00 ታሽጎ በ4 ፡30 ይከፈታል፡፡
ውድድሩ በሎት ወይም በተናጠል ለማወዳዳር ኮሌጁ የተሻለውን አማራጭ ይጠቀማል፡፡
እቃዎቹን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 141 00 31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡
በጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ



Posted: በኩር ግንቦት 17 ቀን 2012
Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page