Sale et medhen10

Sale et medhen10


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ፋማዳ/ ግሥአቡ/020/2012

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ ገጹ (Website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለምድብ አንድ ብር 35,000.00 ( ሰላሳ አምስት ሺ ብር) እና ለምድብ ሁለት ብር 15,000.00 ( አስራ አምስት ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ . ም እስከ ቀኑ 8 ፡ 00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ማለትም ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ . ም በፋሲሊቲ ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ በሚከተለው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ይከፈታል፡፡ ምድብ 1 ከቀኑ 8 ፡ 30 ሰዓት፣ ምድብ 2 ከቀኑ 9 ፡ 15 ሰዓት
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011 551 2400 የውስጥ መስመር 217 ወይም በቀጥታ 011 550 49 31 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page