Sale d/birhan11

Sale d/birhan11


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራከሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ

1ኛ የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
2ኛ የጽዳት እቃዎች ከመደበኛ በጀት በድጋሚ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በ2012 በጀት ዓመት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN Number/ ያላቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ከብር 50,000/ሃምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆኑ የተጫራች እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር1 -3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት በጥቅል ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በከፊል ወይም ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡
ለእያንዳንዱ እቃ የስፔስፊኬሽን መግለጫ መሞላት አለበት፤ ነገር ግን የስፔስፊኬሽን መግለጫው ያልተሞላበት እቃ ቢኖር ተጫራቹ ጽ/ቤቱ የሚፈልገውን ጥራት ያለው እቃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
የሚገዙትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በጨረታው ሰነድ ላይ ማረጋገጫ ያልተቀመጠለት ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ፅሁፍ መኖር የለበትም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮቁጥር 23 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% በባ ንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ጋራንትበስማቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በሚል አድራሻ በስማቸው ከኢርጅናል ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በድጋሚ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ ብ/ ከ/ አስ/ ከ/ ል/ ቤ/ ኮ አገ/ ጽ/ ቤት ግ/ ፋ/ ን/ አስ/ ደ/ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መዋዋልና ሰውሉ መሰረት እቃውን የማጓጓዣ ወጪን ችሎ በደ/ብ/ከ/አስ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ሊቀርብባቸው የሚችሉትን በትክክል ስለእቃው ሊገልፅ የሚችል ስፔስፊኬሽን በፅሁፍ ወይም በፎቶግራፍ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 % 10 በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የሚያስይዙት ዋስትና ጊዜ እቃው ተጠናቆ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም ሰግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ተጫራቶች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0111906580/ 011 681 28 57 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት

ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ ቤት የግዥና

ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012

Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page