Sale con habru kobo1

Sale con habru kobo1


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 06/2012

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ውሃ ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት

የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የውሃ እቃዎች እና በተለያዩ ቀበሌዎች የውሃ ግንባታ በደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ /WC/ እና አርቲዥኖችን ጨምሮ በእጅ ዋጋ፣ ለሀብሩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ ቤት በኦልማ በጀት ለኦሊመንታ ትምህርት ቤት ግንባታ እናለሀብሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለአቢዎት ፍሬ ጤና ኬላ ግንባታ ከ ደረጃ 9 በላይ BC እና GC ተቋራጮች በሙሉ ዋጋ፡፡
ለሀብሩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በአዴጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና በጀት ለጎርፍ መከልከል የወንዝ ጠረጋ ሥራ ለማሠራት ዶዘር 30 5HP የሥሪት ዘመኑ 2012 እና በላይ የሆነው ማሽን ኪራይ፣ ለሀብሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት የመርኮታ ጤና ኬላ መጸዳጃ ቤት እና ለመርሳ ጤና ጣቢያ ኢንስነሬተር በደረጃ 9 እና በላይ BC እና GC ተቋራጮች በሙሉ የእጅ ዋጋ በዘርፉ በተሰማሩበት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በተጠየቁት የግዥ ዓይነትና ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
በውሉ መሠረት ያሸነፈበትን እቃ ግዥ ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
ማስታወቂያ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለምግብ ዋስትና በጀት ማሽን ኪራይ ማስትወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ለኤልማ በጀት ግንባታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን እና ስዋን ዋሽ በጀት ግንባታና እቃ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት የሥራ ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
የጨረታ ማስከበሪ ያ 1% በCPO ያስይዛሉ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመሪያ ለእያንዳንዱ ለጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል የ ዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከሚቆይበት መጨረሻ ቀ ን እስከ 11 ፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለግብርና ማሽን ኪራይበ16 ኛው ቀን እና ለአልማ ግንባታ በ21 ኛው ቀን እስከ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ለዋን ዋሽ ግንባታ እና እቃ በ31 ኛው ቀን እስከ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ለዋን ዋሽ በጀት እቃና ግንባታ በ31 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ለምግብ ዋስትና በጀት ማሽን ኪራይ በ16 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ለአልማ በጀት ግንባታ በ21 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ፖስታውን ከፍተን የምናወዳድር መሆኑ ይታወቅ፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሙሉ አድራሻ፣ ማህተም፣ ፊርማ እና ሌሎች መረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው አሸናፊ ከሆነ 10% የውል ማስከበሪያ CPO ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርብዎታል፡፡
በጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0333330585 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012
Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page