Sale comp tex buil

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ
ቁጥር ጀዊ 027/2012
የጀኔራል ዊንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተለያዩ የስልጠና ግብዓቶችና የቢሮ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች የደንብ ልብስና የማሰፊያ የእጅ ዋጋ በሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለ2012 በጀት ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡
ሎት 1. የደንብ ልብስ ጨርቅ እና ጫማ
ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ
ሎት 3 የኮምፒዩተር እና የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች
ሎት 4 የማሰልጠኛ ዕቃዎች ህንጻ መሳሪያ ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ የአውቶ፣ የቆዳ እና ቴክስታይል፣ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ እና ውድ ወርክ በጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተወዳዳሪ፡
በዚሁ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ
የግብር ከፋይ TIN ሰርተፍኬት
የቫት (VAT) ተመዝጋቢ
በመንግስት ግዢ መሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት (Supplier list) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
1. በተጠቀው ዝርዝር እስፔስፊኬሽንና መለኪያ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫት ማካተትና ዋጋም ሲሞሉ ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው እቃ ሎት ብቻ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቀባቸው እቃዎች አስቀድሞ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተጠየቀውን ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
3. ከላይ ለተገለፁት ሎ ት 1 2000 ብር ሎት2 5000 ብር ሎት 3 5000 ብር ሎት 4 3000 ብር ብቻ ሎት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም CPO በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
4. ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዱሎቶች 50 ብር / ሀምሳ ብር ብቻ / በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኮሌጁ የመንግስት ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ብሎክ 7 መጥተው መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ07/9/2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት እስከ 24/9/2012 ዓ.ም 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በማሸግ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ 24/9/2012 ዓ . ም ከቀኑ 4 ፡ 00 ታሽጎ በእዛው እለት በ 4 ፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ዘግይቶ የሚመጣ ተወዳዳሪ ተቀባይነት የለውም::
7. በጨረታው አሸናፊው ጨረታውን አሸንፎ ውል እስኪፈራረም ድረስ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስለትም በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበት እቃ ኮሌጁ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሱ በትራንስፖርት ወጪ በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ አለበት።
10. አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን እቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ስም ማስያዝ አለባቸው::
አድራሻ፡- ከመድኃኒዓለም የመሰናዶ ት/ ቤት ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ዊንጌት ቀለበት መንገድ ሳይደርሱ ወይም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስትያን አጠገብ።
ስልክ ቁጥር፡- 011 8 59 21 79
የጀኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 07 ቀን 2012
Deadline: June 1, 2020
© walia tender