Sale comp hawassa water sewerage1

Sale comp hawassa water sewerage1


የጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የወጣ

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

የግዥ መለያ ቁጥር ግፋ/09/2012

የሃዋሳ ከተማ መ/ው/ ፍ/አገ/ድርጅት ኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርበው መውዳደር ይችላሉ:: በዚሁ መሠረት የሚፈለጉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡

ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው - የ2012 ዓ/ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ - የተጨማሪ እሴት ታክስ ( የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ግዥዉን በሚፈፅመዉ ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል:: ከተጠየቀዉ ሲፒኦ ማስያዣ ዉጪ ያቀረበ ጨረታው ዉድቅ ይደረጋል፣

የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 | ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ከሃዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግ/ንብ/አስ/ከ/ቲ/አስተባባሪ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣

ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ሠነድ ካልያዙ የጨረታ ዶክመንቱ አይሸጥም፣
የዕቃዎችን ብዛት ተዘጋጅቶ በሚሸጠው የጨረታ ዶክመንት ላይ በዝርዝር ተገልጿል፣

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፣

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11.00 ሰዓት ድረስ ሃዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት ግ/ንብ/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3 ፡ 00 ሰዓት እስከ 8 ፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሃዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 046 212 1580/ 046 22128826 ፖ.ሣ.ቁ.፡- 108 አድራሻ ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር አስፋልት ፊት ለፊት፡፡


የሃዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 13, 2020


© walia tender

Report Page