Sale comp ANRS fin211

Sale comp ANRS fin211


የብሔራዊ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግጭ 03/2012

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ እስካነር እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ማሟት ያስበት፦

በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣ የዕቃ ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ብር ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 በአሥራ አምስት/ ቀናት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50 / ሃምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16 ኛው / በአሥራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው አብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 229 ላይ ይከፈታል፡፡
በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምገሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ አብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ መጋዘን ድረስ ማንኛውንም የትራንስፖርት የማጓጓዣና የጫኝና አውራጅ ወጭ በራሱችሎ በበጀት ዓመቱ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ደረስ ማስረከብ አለበት፡፡
በእያንዳንዱ እቃ/በተናጠል ዋጋ አሸናፊ ሁኖ ይመረጣል።
ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፤ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ቁጥር 226 ወይም 229 በአካል በመገኝት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 77 56 በመላክ በስልክ ቁጥር 058 220 13 56/058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የአብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ባህር ዳር



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012
Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page