Sale bui weliata27

Sale bui weliata27


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


የጨረታ ቁጥር ወዞፋ /012/12

የወላይታ ዞን ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት ለቴሌቪዥን ጣቢያ ስራ የሚሆን ጄነሬተር (30KVA sileneced generator with ATS) በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 40,000 / አርባ ሺህ/  ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከኦሪጅናል የጨረታ ሃሳብ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናሉን በአንድ ላይ በማሸግ እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ20 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ21 ኛው ቀን ከቀኑ በ8 ፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ8 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 21 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

አሸናፊ ተጫራች ላሸነፋቸው እቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ አድርጎ እና ገጥሞ ሲጨርስ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465512116 እና 0461807233 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

***መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ***


የወላይታ ዞን ፋ/ ኢል/ መምሪያ


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 17, 2020


© walia tender

Report Page