Sale bd in tec 23

Sale bd in tec 23


የጨረታ ማስታወቂያ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2012 በጀት ዓመት የፅህፈት መሳሪያ ሃአግ/ባዳቴኢግዥ/ 6/2012 በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ኢንስቲትዩቱ ለሚገዛቸው እቃዎች በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች የስራ ዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራችች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም (ላለማጭበርበር) ቃል የሚገቡበትን ቅጽ (ከጨረታ ሰነዱ መጨረሻ ገፅ የተያያዘውን ቅጽ ፈርመውና ማህተም አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፤ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና ጨረታ እንዲሳተፉ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሁሉንም ሠነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦርጅናል ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአግባቡ ታሽጎ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶችን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ የጨረታ ሰነዱ ይሰጣቸዋል።
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ማስረጃቸውን ከኦርጅናል ፋይናንስ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጃቸው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ስራዎች ማስፋፊያ ጽ/ቤት የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ትችላሉ፡፡
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነቱ ታውቆ ውሉ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ንብረት አስተዳደር እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 ማስገባት ይችላሉ፡፡
የፅህፈት መሳሪያ ሃአግ/ባዳቴኢግዥ/6/2012 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምር በ16 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ፡- ጨረታ መክፈቻና ማስገቢያን በሚመለከት ካሌንደር የሚዘጋው ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡
ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሌላ ተወዳዳሪ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 820 92 64 ወይም 058 226 41 14 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ፋክስ ቁጥር 058-226-41-14



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page