Sale 6

የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት በሶዶ ከተማ አስተዳደር በUIIDP ፕሮግራም የሚገዙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Electronics (SOD/UIIDP/G-1/2012)
1.1 (lot-1) Laptop Computer ብዛት በቁጥር 10.
1.2 (lot-2) Desktop Computers. ብዛት በቁጥር 2.
1.3 (lot3) Printer ብዛት በቁጥር 2.
Furniture (SOD/UIIDP/G-2/2012)
2.1.(lot-1)Chair & Table. ብዛት በቁጥር 15.
2.2 (lot-2) File Cabinet. ብ ዛት በቁጥር 05.
Motor Bike for UIIDP Project Staffs (SOD/UIIDP/G-3/2012). ብዛት በቁጥር 05.
በመሆኑም በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተመዘገቡ፣ ለ2012 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ጨረታው የሚከናወነው፡- ሀገራዊ ሽፋን ባለው ሚዲያ ለ15 ቀናት አየር ላይ በሚቆይ ማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎ በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 28/2010 አንቀጽ 16 (የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አሠራርን) በመከተል ይሆናል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች መረጃዎችን ለማግኘትና የጨረታ ሰነዱን ለማየት ጨረታው አየር ላይ በሚውልባቸው የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ረፋድ 6፡30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የወላይታ ሶዶ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ጉዳይ ቡድን ቢሮ ቀርበው ማነጋገር ይችላሉ።
የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በሶዶ ከተማ ፋይናንስና ኢ/ል ጽ/ቤት መደበኛ አካውንት አካውንት ቁጥር 1000018212335 ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ አምጥተው መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡- የወላይታ ሶዶ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ጉዳይ ቡድን ቢሮ
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይቻላል። ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። 16 ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ( የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና
ለ Electronics(SOD/UIIDP/G-1/2012) 6,000.00 ( ስድስት ሺህ ብር) ፣
ለFurniture(SOD/UIIDP/G-2/2012) 4000.00 ( አራት ሺህ ብር) እና
ለ Motor Bike for UIIDP Project Staffs (SOD/UIIDP/G-3/2012) 6,000.00 ( ስድስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል።
መ/ቤታችን የጨረታውን ሂደት በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ የማራዘም ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-09-10-55-57-01 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21፥2012
Deadline: May 14, 2020
© walia tender