Sale 36

ከጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ / ጽ / ቤት
የተሽከርካሪ ሽያጭ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር 005/2012
ከጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ምክንያቶች ተይዘው የተወረሱ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡- ለጨረታ በቀረቡት ተሽከርካሪ ዎች ላይ ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትየጵያዊ መጫረት ይችላል፡፡
ተሽከርካሪው የሚገኘው በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው::
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን የገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 ( አንድ መቶ) በመክፈል ሪሲት ከወሰደ በኋላ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት የተሽከርካሪ መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል ፡፡
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ከድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ግቢ ነው፡፡
ተጫራቾች ለሚጫረተው ተሽከርካሪ የሰጠውን ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል ፡፡
ተጫራቾች ዋጋ ሲሰጥ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት፡፡
ማንኛውም ተጫራች ዋጋ የሞላበትን የጨረታ ሰነድ እና ለጨረታ ዋስትና እንዲሆን በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ከባንክ ያሰራውን (CPO) በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የኮሚሽኑ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ ም ከጠዋቱ 3 ፡45 ድረስ በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው በእለቱ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ ም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ላይ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሦስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ውጤቱ ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቀርቦ እስከሚፀድቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡
ከላይ በተራ ቁጥር 12 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
ማንኛውም የጨረታ አሸናፊ በጨረታ የገዛውን ተሽከርካሪ ወደ ሌላ አካባቢ ይዞ ለመጓዝ የመንገድ ዳብዳቤ እንዲጻፍለት የጠየቀ እንደሆነ ተሽከርካሪውን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የ3 (ሶስት) ተከታታይ ቀናቶች ብቻ የሚያገለግል የመንገድ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 025112-49 28 መደወል ይቻላል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን
የድ/ ዳ/ ቅ/ ጽ/ ቤት
_______________________________
Category : Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 17፥2012
Deadline :2020-04-02