Sale other biluil tex 25 addis cult turi

Sale other biluil tex 25 addis cult turi



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012

Deadline: June 1, 2020


© walia tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት በጨረታ ቁጥር 001.1//2012 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ለመግዛት የሚፈለጉ ዕቃዎች በጥቅል

የተለያዩ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
አላቂ የፅዳት እቃዎች
አላቂ የመድረክ እና የህንፃ እቃዎች
የመዋቢያ እቃዎች
አላቂ የፅህፈት እቃዎች
የተለያዩ ጥገናዎች
የተለያዩ አልባሳቶች
ቋሚ እቃዎች
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት አራት ኪሎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት በሚገኘው ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱንም ከላይ በተገለፀው ቀን ውስጥ በመመላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን አይነት በመፃፍ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መመላት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች አንዱንም ወይንም ሁሉንም ለማቅረብ መወዳደር ይችላሉ የጨረታ ሰነዱን ሊያስገቡ የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ያስያዙት ናሙና የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ ይመለስላቸዋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
በጨረታ ለሚያሸንፉባቸው ዕቃዎች የመልካም ስራ አፈፀጸም የሚሆን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10 ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 6 ፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 7 ከቀኑ በ7 ፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-245441 ወይም 0111-225944 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሕፃናትና ወ ጣቶች ቴአትር

Report Page