Sale 2

የጨረታ ማስታወቂያ
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞቸ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የመኪኖቹን/ንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች እስከ አርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሽከርካሪዎቹን በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ፡1.1 በአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ ቃሊቲ ኖክ ማደያበሚድሮክ ተርሚናል ወደ ውስጥ 1.5 ኪ.ሜ ገባ ብሎ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ቅጥር ግቢ፣ 1.1 ቃሊቲ ኪዳነምህረት መኪና ማቆያ 1.2 መቀሌ ቅርንጫፍ 1.3 ሀዋሳ ቅርንጫፍ
ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪዎቹን/ንብረት ዝርዝር የያዘውንፎርምይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቦሌ ሩዋንዳ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ሕንፃ በሚገኘው በኩባንያው ዋናው መ/ቤት ወይም ከላይ በተራ ቁጥር 1.1 ላይ በተገለፀው ስፍራ በመገኘት እስከ አርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾችሙግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስ ከ አርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% ( ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ(CPO) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
ጨረታው ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት ቦሌ ሩዋንዳ በአፍሪካኢንሹራንስ ኩባንያ ዋናው መ/ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ በ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በመከፈልማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ቀናት በየቀኑ 100.00 (አንድ መቶ ብር) የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
ለጨረታ በቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈሉ ይሆናሉ፡፡
መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116610491 እንዲሁም ለመቀሌ ተጫራቶች በስልክ ቁጥር 034440-1932 በመደወል ወይንም በኩባንያው ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን እንዳለበት መሆኑን እንገልፃለን
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 8, 2020
©walia tender