Sale 1

የጨረታ ማስታወቂያ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/23/SC/2012
ስኳር ኮርፖሬሽን ለ2013 ዓ.ም. አጀንዳና የጠረጴዛ ካሌንደር ሕትመት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2 . ጨረታው ግንቦት 6 2012 ዓ . ም . ከቀኑ በ 8 ፡ 00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ግንቦት 6 2012 ዓ . ም . ከቀኑ በ 8 ፡ 30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
3 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4.ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን
ግዥና ሎጀስቲክስ
ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ
ኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጀርባ ባለው አዲሱ ሕንፃ 4 ኛ ፎቅ
ጆሴፍ ቲቶ መንገድ
ስልክ ቁጥር 0115500569
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 ( አስራ አምስት ሺህ ብር) ፤ በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡
8.ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስኳር ኮርፖሬሽን
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21፥2012
Deadline: May 14, 2020
© walia tender