Sale 1

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/በስልጤ ዞን የዳሉቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች
ሞተር ሳይክሎች
የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች
የመኪና ጎማዎች
ኤሌክትሮኒክሶችን ለመሸጥ ይፈልጋል
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000/ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ፤ ቢድ ቦንድ ማስያዝ የሚችል፤ ከዳሎቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ለሰነዱ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን አያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ፤ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በዳሎቻ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት ይኖርቦታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡
ተጫራቾች የዕቃዎችን አይነት ዳሎቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት ሰአካል መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተወዳዳሪዎች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጥም
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ 0464660141/142 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የዳሎቻ ወረዳ ፋይ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17፥2012
Deadline: May 15, 2020
©walia tender