Safaricom Ethiopia

Safaricom Ethiopia

Tewdaj Eshety

#ETHIOPIA

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Ecoonomic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። 

በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ መሪነት በመገኘት የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው “ወደገበያ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ባለበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገልን አበረታች ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በኢትይጵያ ድንቅ አቅም እንዳለ ተመልክተናል። ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስነምህዳር መገንባትን እንቀጥላለን” ብለዋል። 

ማቲው ሀርቪ-ሀሪሰን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ እና ፔድሮ ራባካል የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና የቴክኖሎጂ ኃላፊ በበኩላቸው ሁሉም ዜጎች ከዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ለመሥራት የገቡትን ቃል ለመፈጸም ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋርም የጋራ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖር ለማድረግ ለዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎች እና ኔትወርኩን በጋራ ለመገንባት የዝግጅት ሥራዎች ላይ ትኩረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። 

በዕለቱ የሳፋሪኮም ኃላ/የተ/የግ/ማ የአዳዲስ ንግድ እንቅስቃሴዎች ኃላፊ ፖል ካቫቩ MPESA ለኬንያ እእና ለሌሎች የ አፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ እድገት የተጫወተውን በማስረዳት በኢትዮጵያ ለሚሠራው ሥራ እንደመማሪያ የሚወሰድ መሆኑን አሳስበዋል። 

ፔድሮ ራባካል የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና የቴክኖሎጂ ኃላፊም የመሠረተ ልማት ዝርጋታው የዋጋ ተመጣጣኝነትንና የግንኙነት ተደራሽነትን ለሁሉም እንደሚያቀርብ እና ሁሉንም የኢንዱስትሪው አካላት ያካተተ፣ በመደጋገፍና ተጠቃሚነት በሚረጋገጥበት ሁኔታ ሥነምህዳሩ እንደሚገነባ ገልጸዋል።  

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የኔትወርክ እና የአይሲቲ መሳሪያዎችን ለማዳረስ እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት በተለይም ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን በተደረገለት ቀና ትብብር መደሰቱ በ አጽንዖት ተገልጿል።  

የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመንግስት አካላት፣ ከልዩ ልዩ አገራት የተውጣጡ ተወካዮች ፣ትልልቅ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢዎች እና የዲጂታል ባለሙያዎች የሚገኙበት ዓመታዊ ጉባኤ ሲሆን በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ለሦስት ጊዜያት ተካሂዷል። በ18ኛው ጉባኤም 240 ተሳታፊዎች ከሰላሳ አገራት ተሳትፈውበታል።

Credit : Tewodaj Eshetu

@tikvahethiopia

Report Page