SW CLUBS

SW CLUBS

DOCH HD

የክልሉ ተወካይ ጊምቦ ዳዲበን 2ተኛ የምድብ ጨዋታውን 2ለ0 አሸነፈ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን በኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከወከሉት ሁለት ክለቦች አንዱ የሆነው ጊምቦ ዳዲበን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን አሸንፏል።

በዛሬው እለት ረፋድ 3 ሰዓት ላይ በተደረገው የምድብ ጨዋታው ጊምቦ ዳዲበን የሲዳማ ክልል ተወካዩን ዳራ ቃባዶ አቻውን ገጥሞ 2ለ0 ማሸነፍ መቻሉን ዶች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የጊምቦ ዳዲበን የማሸነፊያ ግቦችን ብሩክ ዳንኤል በ18ኛው ዲቂቃ እንዲሁም ተሻገር ክፍሌ በ87ተኛው ደቂቃ ያስቆጠሩ ሲሆን ክለቡ ነጥቡን 4 ማድረስ ችሏል።

ሌላኛው የክልሉ ተወካይ ማሻ ወረዳ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከዶንቦስኮ ዓድዋ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን አድርጎ 2ለ1 ተሸንፏል። ክለቡ በመጀመሪያ ጨዋታው ነጥብ መጋራት መቻሉ የሚታወስ ነው።

ዶች

Report Page