SOFT 7

SOFT 7

አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)

የጨረታ ማስታወቂያ 

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር (EVA) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ አንድ (01) የዌብሳይት ሰርቨር (Website Sever) ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ማህበሩ በአክብሮት ይጋብዛል:: 

  1.  የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ስለመመዝገባቸው የምስክርነት ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣ 
  3. በመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በዘርፉ አቅራቢነት ስለመመዝገባቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፣
  5. . ከላይ ከ1-4 የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉና የተጠየቁ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የማይመለስ 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አሥር) ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር (EVA) ቢሮ ቁጥር 303 ወይም 306 ዘውትር በሥራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 10:00 ድረስ ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ማህበሩ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለጸው ዝርዝር (Specification) መሠረት ዋጋቸውን ከVAT በፊት እና በኋላ በግልጽ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለማሕበሩ ማስገባት አለባቸው::
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ጥሬ ገንዘብ ወይም ሕጋዊ ቼክ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያኑ ይመለስላቸዋል። .
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም። 
  10. አሸናፊው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃዎቹን እስከ ማህበሩ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል። 
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ +251-115-525O20 (118-697-868) ወይም 0940-086-194 መደወል ይቻላል። 

አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ፊት ለፊት 500 ሜትር ገባ ብሎ ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ፣ ይመናሹ ሕንጻ አጠገብ 

የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር 

 Posted date:ሪፖርተር መጋቢት 13፥2012

Dead line:April 1,2020 (መጋቢት 23)


See related tenders

Back

Report Page