SNNPRS

SNNPRS


#ደቡብ_ክልል

አንደኛ በመኸር ዝናብ መዛበት ሁለተኛ በግጭት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች መጨመር በደቡብ ክልል የተረጂዎችን ቁጥር ጨምሯል።


የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንደሚለው፤ አሁን ላይ በደቡብ ክልል 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፋ ረሃብ / የምግብ ዋስትና ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል ተንብዩዋል። 


የከፋ ለሆነ የምግብ ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ የተባሉት ከዚህ ቀደም የምግብ ችግር ኖሮባቸው በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሲደገፉ የነበሩ (917 ሺህ)፣ በግጭት የተፈናቀሉ (122 ሺ) ፣ በመኸር ዝናብ መጥፋት ምርት ያላገኙ (2.3 ሚሊዮን) ነዋሪዎች ናቸው።


በደቡብ ክልል የከፋ የምግብ እጦት ካለባቸው አካባቢዎች አንዱ የኮንሶ ዞን ህፃናት እና እናቶች ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸውን ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።


በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት እየደረሰ እንዳለሆነ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።


የኮልሜ ክላስተር ነዋሪዎች ፦


" ምንም አይነት እየመጣ አይደለም። ምንም አይነት ድጋፍ አላገኘንም። እኛ መጠበቅ ካለብን መንግሥት እንዲደርስልን ነው። ከሞት እንዲታደገን ነው። በገንዘብም ቢሆን መንግሥት እንዲረዳንና ከዚህ ዓመት ቢያሻግረን ብለን ነው የምንማፀነው። "


ሌላ ነዋሪ ፦


" አንደኛ ዝናብ ጠፋ ፣ በዛ ላይ የከብት ሳርም የለም። በመንግስት በኩል የሚደረግ እርዳታም የለም " ብለዋል።


የኮንሶ ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፈኔ ቲጫኖ በዞኑ ካላት ተረጂዎች እስካሁን ድጋፍ ያገኙ ግማሽ እንኳን እንደማይሆኑ ተናግረዋል።


በተለይ ከሀምሌ ወር ጀምሮ የምግብ ድጋፍ ፈላጊው ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል።


አቶ ከፈኔ " የበልጉ ዝናብ ጥር 9 እና 10 ዘነበ ከዛ በኃላ መጋቢት ላይ ሁለቴ ዘነበ ከዛ በኃላ ዝናቡ አቆመ ምርት አልሰጠም። እኛ እያሰብን ያለነው በበልጉ ምርት ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ አርባ አራት ኩንታል ለማምረት ነው። ነገር ግን አሁን ሲሰራ ሊገኝ ይችላል ተብሎ የታሰበው አራት መቶ ሰባስድስት ሺ ስምት መቶ ሰባ አራት ምርት ነው የሚገኘው ያ ማለት 16% የዞኑን ህዝብ ይመግባል። ቀሪው አንድ መቶ ዘጠና ሺ ስምንት መቶ ሀያ አምስት ዜጎች ከሀምሌ በኃላ ሊራብ ይችላል የሚል ግምገማ ነው ያለን " ብለዋል።


በኮንሶም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የደቡብ ክልል አካባቢዎች የምግብ ድጋፍ አልደረሰንም በሚል ከነዋሪዎች በሚነሳው ዙሪያ የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፋሲካ አለሙ " ከፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር communicate እያደረግን በተቻለ መጠን ችግር ውስጥ የሚገቡ ካሉ ምግብ እያቀረብን እየሄድን ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ ክልላችን ከምግብ ዋስትና ከሪሊፍ እና ከሴፍቲኔት ፕሮግራም አኳያ በተሻለ መልኩ የሚመጡ አቅርቦቶች፣ ድጋፎች ለታላሚው የህብረተሰብ ክፍል የሚደርስበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው። ይህ ማለት ግን ሁሉንም ተረጂ እና ተጎጂ ባለን ውስን resource እንደርሳለን ማለት አይደለም። ምናልባትም miss የሚደረጉ ነገር ግን ማህበረሰቡ ከራሱ ካፒታል፣ በራሱ አቅም እርስ በእርስ መደጋገፍ የሚችልበት ስርዓት ስላለ በሀገራችን በእዛ መልኩ ሊሄድ የሚችልበት ሁኔታ እንዲፈጠር በሌላ በኩል መንግስት ባለው አቅም የተቸገረ የተራበ ዜጋ እየደገፈ የሚሄድበት እድል እየፈጠርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው " ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ነው።

Report Page