#SA
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በርሳቸው አመራር ወቅት የተፈፀመውን የሙስና ጉዳዮች ለሚያጣራው ቡድን የምስክርነት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ የሞት ማስፈራሪያ ለሳቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
ዛሬ ሐምሌ 9፣2011ዓ.ም የማጣራት ስራውን ለሚመሩት ዳኛ እንደተናገሩት ማስፈራሪያው የደረሳቸው ሐምሌ 8፣2011 ዓ.ም የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተከትሎ ነው ብለዋል።
በዚሁም ቀን በሰጡት የምስክርነት ቃል የመግደል ሙከራ እንደተሞከረባቸው አሳውቀው ነበር።
በባለፈው ዓመት ከስልጣን በኃይል የተወገዱት ጃኮብ ዙማ ስልጣናቸውን ያላአግባብ በመጠቀም ሙስናን ፈፅመዋል የሚሉ ውንጀላዎች ቢቀርብባቸውም እሳቸው ግን ክደዋል።
ጃኮብ ዙማን ተክተው ወደ ስልጣን የመጡት ምክትላቸው ሲሪል ራማፎሳ በበኩላቸው ሙስናን ለመታገል ቁርጠኝነት እንዳላቸው ቃል በመግባት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን ዘጠኝ አመት የስልጣን ቆይታም የባከነ ጊዜ ብለውታል።
ሰኞ ዕለት የ77 አመቱ ዕድሜ ባለፀጋ ጃኮብ ዙማ የቀረቡባበቸው ውንጀላዎች እሳቸውን "ከፖለቲካው እይታ ለማጥፋት የተቀነባበረ" ነው ብለውታል።
በዛሬው ዕለትም ጃኮብ ዙማ ለዳኛው እንደገለፁት ረዳታቸው እሳቸውንና ልጆቻቸውን እንደሚገድሏቸው የሚገልጽ የማስፈራሪያ የስልክ ጥሪ መቀበሏን አስረድተዋል።
'ስቴት ካፕቸር' የተሰኘው ምርመራ ጃኮብ ዙማ አወዛጋቢ ከሚባለው ቱጃር የጉብታ ቤተሰብ የነበራቸውን ያላግባብ ግንኙነት፤ እንዲሁም ስልጣናቸውን በመጠቀም ከፍተኛ የአገሪቱ ሚንስትሮች በአገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔ ጫና ማሳደርና ከፍተኛ ጨረታዎችን በሙስና ማሸነፍን ይመለከታል። ሁሉም አካላት ውንጀላውን አይቀበሉትም።
"የሙስና ንጉስ ተደርጌ በሰዎች ዘንድ እንድጠላ ተደርጌያለሁ" በማለት ሰኞ እለት ለዳኛው ሬይ ዞንዶ ተናግረዋል።
በደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን ለማምጣት በሚጥሩበት ወቅት አሜሪካና እንግሊዝ ለአመታት አሁንም እሳቸውን ለማሳጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ሌሎች ከውጭ የመጡ የሰለጠኑ ወኪሎች ሊመርዟቸው እንደሞከሩም ጨምረው ተናግረዋል።
Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia