Retail Liberalization

Retail Liberalization

Ethiopianbusinessdaily

የችርቻሮ ገበያው ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ቢሆን (Retail Liberalization)....

የሀገር ውስጥ ነጋዴ ዓለም አቀፍ ብራንድ የሆነ ምርት አስመጥቶ በመሸጥ እና አምራቹ እራሱ በሀገር ውስጥ ሱቅ ከፍቶ መሸጥ ቢጀምር ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


#ለምሳሌ፦ ኦርጅናል Nike የሚያስመጣ የኢትዮጵያ ነጋዴ ሱቅ ከፍቶ መሸጥ ይችላል/ይፈቀዳል! ነገር ግን የአሜሪካው የNike ጫማ አምራች ኢትዮጵያ ውስጥ ሱቅ ከፍቶ ምርቱን መሸጥ አይችልም/አይፈቀድም!


ልዩነቱ ምንድን ነው?


መሰረታዊው ምክንያት #የችርቻሮ_ገበያን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ያለማድረግ የፖሊሲ መነሻ ሲሆን ነገር ግን የማምረት እና ለውጪ ገበያ ብቻ ማቅረብን ግን ያበረታታል። ለዚህ ደግሞ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት/ጥበቃ ለማድረግ (Protectionism) እና የካፒታል/የውጪ ምንዛሬ ወደውጪ ሀገር የሚኖር ፈሰስን ለመከላከል ነው።


#ለምሳሌ፦ የNike ጫማ ከውጪ አስመጥቶ የሚሸጥ የሀገር ውስጥ ነጋዴ ግብይቱ በኢትዮጵያ #ብር ከመሆኑ በተጨማሪ የአስመጪነት አስገዳጅ የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ ላያደርግ ይችላል! ነገር ግን የውጪ ድርጅት ጫማ ለሸማቹ በብር ቢሸጥም በሂደት ከብሄራዊ ባንክ በምትኩ በዶላር/በውጪ ምንዛሬ እንዲለወጥለት መጠየቁ አይቀርም (የዓለም የንግድ ድርጅት ከአስገዳጅ ህጎቹ መካከል ነው! የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የአስገዳጅ ህጉ አስገዳጅ አስፈፃሚዎች ናቸው)።


በተለያየ ምክንያት ተፎካካሪ ምርት ለማቅረብ የሚቸገረው የሀገር ውስጥ አምራች የተሰጠውን የጥበቃ ፖሊሲ ባለመጠቀሙ ገበያው በተዘዋዋሪ የከውጪ አስመጪዎች ሆኗል (ደካማ የደጋፊ ፖሊሲ አማራጭ መኖር፤ የምርት ጥራት እና የማምረቻ ወጪ ዝቅተኛነት ይህንን ሁኔታ አግዘውታል)።


ቸርቻሪዎችን በሀገር ውስጥ ገበያ የማስገባት ሁኔታ ከ1990ዎቹ ጀምሮ ባሉ ጥናቶች አዎንታዊም አሉታዊም ውጤት ማምጣቱን ያሳያሉ (የምርት ጥራት፤ የዋጋ ምክንያታዊነት፤ የሰራተኛ ደሞዝ እና የገበያ ስልት መሻሻል ሲፈጠር አነስተኛ የሀገር ውስጥ አምራቾች መዳከም መከሰቱን አሳይቷል)።


ኢትዮጵያ ውስጥ የችርቻሮ ገበያ ለውጪ ባለሃብቶች የመክፈት (Retail Liberalization) ሃሳብ መኖሩ ተገልጿል (በጠቅላይ ሚኒስትሩ) ይህን በተመለከተ የኔ ሃሳብ አነስተኛ አሉታዊ ጎን ብቻ ነው የሚታየኝ....


1. የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በብዙ ዘርፍ በሩን የዘጋበት ምክንያት በጣም አሳማኝ ነበር ለማለት ያስቸግራል (ሲያከራክር የኖረው የቴሌኮም ገበያ ሲከፈት ውጤቱ አሉታዊ አይደለም!)፤ ከሪፖርቶች ተነስተን ከተመለከትን ላለፊት 30 ዓመታት የባንክ ሴክተሩ የመሮጫ ሜዳው ከውጪ ጫና ተጠብቆም ከከተማ ለመውጣት አልደፍር ብሏል፤


2. በጥበቃ ውስጥ ያሉ የሀገር ውስጥ አምራቾች በተለያየ በራሳቸውም ሆነ በመንግስት ችግር በኢኮኖሚው በዋጋ፤ በጥራት እና በመጠን የምርት ፍላጎትን ለማርካት ተቸግረው Import በገበያው ነግሷል፤


3. በአነስተኛ የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ፋይዳ በትንሹም በትልቁም በሩን ለውጪ ገበያ በመዝጋቱ ዓለም አቀፍ ጫናው ለጠቅላላ ኢኮኖሚው የሚገባው አይደለም፤


4. ኢኮኖሚው ከፖሊሲ ይልቅ የአምራቾች እና የአስመጪዎች የገበያ ትንበያን ተከትሎ የሚሄድ ሆኗል (ለኢንዱስትሪ የታለመው ኢኮኖሚ በአገልግሎት ዘርፉ ጥላ ስር አርፏል)፤ ወዘተ


ማሰብ የሚያስፈልገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ካዝና የማይገመት አይደለም (ካፒታል በተፈለገ ፍጥነት ወደ ውጪ ምንዛሬ የሚለውጥ ሊሆን አይችልም)፤ የዜጎች የዓለም አቀፍ ብራንዶች የመሸመት አቅም ሁኔታ፤ ሌሎች አሳሪ የፖሊሲ እና የፖለቲካ ሁኔታ ተደራርቦ በውጪ ቸርቻሪ ገበያተኞች ገበያው ይጥለቀለቃል የሚል ግምት የለኝም።


ስለሆነም የውጪ ቸርቻሪዎች አጋዥ ፖሊሲዎችን መጠበቃቸው ካለመቅረቱ (የውጪ ምንዛሬ በገበያ መወሰን፤ የፈጠራ መብት ጥበቃ፤ ወዘተ) በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አነስተኛ አምራቾችን ከተፎካካሪት በላይ የማምረት አቅማቸውን የሚፈትነውን ችግር ለመፍታት ጥረት ቢደረግ መጥፎ እርምጃ እና የሚታይ አሉታዊ ውጤት ኢኮኖሚው ላይ ያመጣል ብዬ አላስብም።

Report Page