Reflections on Psalms 32
Pursuing Holiness
ዳዊት በዋናነት ሀጥያቱን ለመናዘዝ ብቻ ከዘመራቸው የንስሀ መዝሙሮች መዝሙር 32 ይለያል። For starters it begins after he repented to bask in the joy of being forgiven. የነበረበትን ሁኔታ በ3 ቃላት ይገልፃል። መተላለፍ፣ ሀጥያት፣ በደል። አንድ በአንድ ቢፈቱ በውስጣቸው አመፅን፣ አለመታዘዝን፣ አቅጣጫን መሳትን ተጠያቂነትንና የፀፀትን ስሜት ሁሉ ይሸከማሉ።
የእኛ ዘመን ሰው ጥፋት እያጠፋ እጅከፍንጅ ተይዞ እንኳን የሚቀናው ቢችል ጥፋቱ ቀላል እንደሆነ ለማሳመን መጣጣር አልያ ደግሞ ቅጣት እንዳይበረታበት ሰበብ አስባብ በመደርደር ማስተባበል እንጂ እንቅጩን ለመካድ ሳይሞክር የተወዘፈበትን ማጥ በተለያየ ቃላት አብራርቶ ራሱን አያስበላም። ምናልባት በእውቀት ደረጃ ስለ አጠቃላይ ብክለት ብዙ እያጣቀስን እናብራራ ይሆናል..
But on a personal level, we downplay how broken we are. I am scarred and stained in every faculty of my being. I was born in sin and inequity. I'd be a fool to assume that I didn't have the capacity to do the most egregious evil a fallen human is capable of doing. When I'm naive enough to think that I have my best intention at heart instead of recognizing that the heart is decietful above all else.. ከጠላቴ ጋር እንደምኖር በዘነጋሁ ቁጥር ውድቀት መንሸራተቴ ይበረክታል።
ዳዊት ውድቀቱን ካብራራባቸው ቃላት በላይ የሚያስገርመው ከዚህ ሁሉ ጥፋተኝነት የገላገለውን መፍትሄ ለመግለፅ የመረጣቸው ቃላት ናቸው። በሚያስደንቅ ሁኔታ ይቅር መባል፣ መሸፈን እና ነፃ መውጣት (የበደል አለመቆጠር) አለ። እነዚህ ቃላት ቢብራሩ የሀጥያቱ ፀፀት ጫና አጉብጦት የነበረው ሰው ሸክሙ ሲራገፍለት ያለው እፎይታ፣ በሀፍረት ሲያሸማቅቀው የነበረው ሁሉ ገለል ሲል፣ እንደሌለ እንዳልነበረ ተቆጥሮ ሲተውና በህግ እንኳን ሊቀጣ ቢጠራ የሚያስከስሰው ጥፋት ላይኖር ዕዳው ሁሉ ተከፍሎ በነፃ የተለቀቀ ሰውን እንድናስብ ያደርገናል።
So its not about merely getting an emotional relief. (Unless emotions are a the effect of mercy and forgiveness, they could be a distraction.) The main objectives of such confession is to receive legal acquittance which has been objectively secured for us in what Christ has accomplished on the cross.
የተገኘው ንፅህና ውጤታማ እንደሆነ የሚያሳየን ደግሞ አስከትሎ ሽንገላ እንደሌለበት በመግለፅ ደስታውን በአግራሞት መግለፁ ነው። እውነትም ከዚህ የሚልቅ ብፅዕና የለም። ምህረት ከበዛለት ላይ እድለኛስ ማነው? ንስሀና ኑዛዜ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት የማደስ ሀይል ያለው ፍቱን መድሀኒት ነው። Keller says we can't experience God without it. And what an immense blessing it is that we can actually confess our sins knowing that He is faithful and righteous to grant us forgiveness.
The Power of Guilt
የበደል ፀፀት አካልን፣ አዕምሮን፣ መንፈስን ሁሉ ያሳምማል። እርግጥ በደላችንን ስንላመደው ህሊናችን ይደነዝዝ ይሆናል ነገር ግን ይህ ነው የማንለው ከምንም ጋር የማይገናኝ በእንቅልፍና ምግብ የማይመለስ ድካም ሀይላችሁን ሁሉ አሟጦት በሌላ መዝሙር "ከመከራዬ የተነሳ ጉልበት ከዳኝ አጥንቴም በውስጤ ሟሟ።" እንዳለው we will start to feel our bones wasting away.
አካላዊ ብቻ አይደለም ደግሞ አዕምሮው ያለእረፍት ቀን ከሌት obsessively ሲያስብ ዝሏል። We can also realize if we look into the words used to describe the state of sinfulness..sin is a direct offense against God so it will create the sense of alienation or separation from God.
እግዚአብሔር በእኛ disappointed ሆኖ እንዳዘነብን ስናስብ በመግቦቱ ለእኛ በጎ ብቻ የሆነው የሚያኖረን እጁ ከብዶ ይሰማናል። በዚህ ልክ በሀጥያት ምክንያት miserable መሆን የአባት ነው። ምንም የማይመስለን ጊዜ ነው እንደውም ደንገጥ ማለት ያለብን።
ኑዛዜ ምንድነው ለሚለው ጥያቄ ከቁጥር 5 በላይ ግልጥ ማብራርያ የለም። Achnowledging what we've done. እንቅጭ እንቅጩን ማሳወቅ። ስንሰራ ያላፈርነውን ድርጊት ስንፀልይ ለመጥራት ሳንሸማቀቅ (ወይንም መሸማቀቃችን እንዳንናዘዝ ሳያደርገን) ስለዚህ ከላይ እግዚአብሔር ሀጥያቱን ሲሸፍንለት ያደረገውን ተቃራኒ ዳዊት እራሱን በማጋለጥ የሰራውን ወንጀል እየዘረዘረ ራሱ ላይ ሲያቃጥር እናገኘዋለን።
One way to understand inequity is the element of being twisted, bent and broken due to the sin thats committed. በእግዚአብሔር ፃዲቅ መመዘኛ የምንታየው ሰባራ እና ጠማማ ሆነን ከሆነ ያንን ለመሸፋፈን በምናደርገው ሙከራ ሌላ ጥመት ውስጥ ከመግባት ሌላ አንዳች አናተርፍም።
So its better to snitch on yourself of all the crimes you've committed against God. Turn yourself in. Surrender. Not because you somehow believe you can pay for it. No, the payment was already dealt with at the cross so run to him and rid of your guilt. Like Christian did at the sight of the cross (in The Pilgrims Progress book)
ኑዛዜያችን ላይ መኖር የሌለባቸው ነገሮች መሀከል : ጥፋትን በሌላ ማላከክ (Shifting the blame)፣ ሰበብ አስባብ ማብዛት (excuses) ፣ በምክኒያት እያስረዱ ማስተባበል (rationalization)፣ የኑዛዜውን ከባድነት ሽሽት በጊዜያዊ ደስታ ሽመታ በደልን ማብዛት (Hiding in temporary pleasures to avoid the pain of confession) ፣ cynical በመሆን ሁሉንም ሰው ያለን አመለካከት የተመታ ማድረግ (We feel better about ourselves if everyone is just as horrible as we are) ፣ ፍፁም ሆኖ ለማካካስ መጣጣር ወይንም ደግሞ እጅግ በጣም በመቆዘምና ራስን በመግረፍ በደለኝነት ውስጥ መክረም አሉበት።
If you expose your sin, God will cover it. This is what emboldens us to be seen. You cant restore what you lost. You dont have to carry your shame or commit more sin on purpose to increase your sentence. Abandon the fig leaves. ሀፍረታችንን ተሸክሞ እርቃኑን የተሰቀለ አዳኝ ስላለን ዘላቂ የሆነውን የእርሱን ፅድቅ እንልበስ እንጂ ቅጠል ለማገልደም አንሯሯጥ።
This can only happen when we're honest. ሽንገላን መተው አለብን መጀመርያ። የሀጥያታችንን አደገኛነት ከማመንና ከማጋለጥ እንጀምር። ከዚያም የምህረት አምላካችን ዘንድ እንደበቅ። እርሱ መሸሸጊያ ነው። ከእርሱ ፅድቅ በስቲያ የሚሸፍነንን ስንፈልግ ስለሰበሰብናቸው የፅድቅ ስራዎች ሳይቀር መናዘዝ አለብን። Our attempts to atone for our sins and be clean on our merit is evil in His eyes. Repent for all the motives you're aware of that offends Him.
ኑዛዜያችን ግኝ እንደበቅሎና ፈረስ በቅጣት ፍራቻ አይደለም መሆን ያለበት። ዉዳችንን መበደል ሊሰብረን ይገባል። ፈረሶች የሚጎትታቸው ልጓም ከሌለ እንደሚገግሙ የግድ ውጫዊ መከራ እስኪገራን አንጠብቅ። ቀን ሳለ፣ በምቹ ጊዜ፣ አሁን በፈቃዳችን እንመለስ። We know enough about Him to willingly submit and obey even when there is no external pressure. We dont have to be dragged like a horse.
Dont take sin lightly cause sin tortures both body and soul. Dont resent Gods heavy hand of conviction. (ዝም ሲለን ነው መፍራት) Abandon all the futile effort to hide from the only hope you have. Run to Him to find a true and eternal hiding place knowing that whether you feel forgiven or not, Gods declaration of your position is whats decides your lot.
And if you're drowning in the feeling of grief and guilt, don't dwell in your misery. Let that pain rush you to confess and then rejoice in the immediate pardon he so graciously grants.
የጠላትህን ክስ ሊደመስስልህ
ከአብ ዘንድ የቆመ ጠበቃ አለልህ
የኃጢአትህን ሸክም ተናዘህ እረፈው
በደሙ ያጥበዋል ለኢየሱስ ንገረው....
በእድፋሙ ልብስህ ሰውነትህ ተከድኖ
በሀፍረት ተውጠህ በደልህ ተጋንኖ
ምንም ነገር ቢሆን ከቶ ተስፋ አልቆርጥም
ብለህ ተሟገተው ከፀጋው አልሸሽም...
ጠላትህን ጥሎ እስራትህን ቆርጦ
ክስህን ደምስሶ ፍርድህን ለውጦ
ያ የፍቅር አምላክ ምህረትን አውጇል
ልብስህም እንዲቀየር ትዕዛዝን አውጥቷል
ደስ ይበልህ ወንድሜ ከሳሽህ ተጥሏል!
የኃጢአትህ ዋጋ በጌታ ተከፍሏል።
ምህረቱን ተቀበል ኃዘንህን እርሳው
ከንስሐ ወዲያ ልብህን ደስታ ይሙላው።
ተስፋዬ 🖤