Psalms 106

Psalms 106

Pursuing Holiness

መዝሙር 105 እግዚአብሔር ስለሰራው ስራ ከተናገረ በኋላ የእግዚአብሔር ህዝብ በአፀፋው የመለሰውን በ መዝሙር 106 እናያለን። ታሪክን በአጭሩ ከማስቀመጡ ባሻገር ስለሰው ልጅ አመፅና ውድቀት እንዲሁም የእግዚአብሔርን የማይለወጥ ታማኝነት የሚያንፀባርቅ ውብና ሀቀኛ ፀሎት ነው።

1. ምስጋና እና ልመና (ቁጥር 1–5):

እንደማንጨርስ እያወቅን የምንጀምረው ምስጋና የእግዚአብሄር ብቻ ነው። ይህ ብዙ ታሪክን የመዘገበ መዝሙር የሚጀምረውም የሚያበቃውም በተመሳሳይ መንገድ ነው። ምስጋና።

ይህ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብም ሆነ ልመናችንን አስታውቀን ወደ ተለያዩ ተግባሮቻችን ከመመለሳችን በፊት ሊኖረን የሚገባውን የልብ ሁኔታ / attitude ይደነግግልናል። አመስጋኝነት የሆኑ የትሁት ሰዎች መገለጫ የሆነ ልዩ የፀጋ ስጦታ ብቻ አይደለም።

አንዳች በጎ ነገር የማይገባው ነገር ግን በለጋስ ምህረት እልፍ መልካምነትን የተቸረ ክርስቲያን ፥

እንኳን ቅዱስ ስሙን ልንጠራ ፥ ልናውቀው እንኳ ያልተገባን ርቀን የነበርነውን ህዝብ ልጅ አድርጎን ያለመሸማቀቅ ልናናግረው/ ልንፀልይ መቻላችንን ስናስብ ከልባችን ሊፈስስ የሚገባው ቋንቋ ምስጋና ብቻ ነው።

በዚህ መዝሙር ላይ የሚዘረዘሩት ማመስገኛ ምክኒያቶች መሃከል የእግዚአብሔር ቸርነት፣ ዘላለማዊ ምሕረት፣ ሙሉ በሙሉ ተቆጥሮ የማያልቅ ታላላቅ ስራን መስራቱና እንደ እርሱ ጽድቅን ለሚያደርጉ የሚያዘንበው ብፅዕናና በረከት አሉበት። ደስ የሚለው እግዚአብሔር በማንነቱ የማይለወጥ ስለሆነ እነዚህን ምክኒያቶች አሁንም እውነት ናቸው። በታሪክ መሀል አልዋዠቁም። ለዘለዓለም የምናመሰግንባቸው ሰበቦች ሊሆኑን ተፅፈውልናል።

ከዚያ የማንጠብቀው ግሩም ልመና አለ

"እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤ ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣ በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው።"

Spurgeon በዚህ ቁጥር ላይ ከመስበኩ በፊት እንዴት እንድንፀልይ እንደማናውቅ ተረድቶ ትክክለኛ ቃላቶችን የሰጠንን የእግዚአብሔር ርህራሄ ያመሰግናል። 

ይህ ፀሎት ቅዱሳን ሁሉ ያላቸውን በረከት ለመካፈል ይለምናል እንጂ ከእግዚአብሔር የተለየ በረከት ይገባኛል ብሎ አይጠይቅም። ቃል ያልተገባልንን ቀላልና ህመም አልባ ህይወት ለመኖር፣ ወይ ፍፁም ለሆነ ጤንነት እየተማፀነ አይደለም።

ሀጥያት አልባው የእግዚአብሔር ልጅ መከራን ከተቀበለ Who am I that I should never be poor or sick? ከኛ በብፅዕና በብዙዙዙ የሚሻሉ ቅዱሳን እንኳን በመከራ ኖረው ወደእረፍታቸው በብዙ ትግል ከገቡ.. አልጋ በአልጋ በሆነ መንገድ በፅጌሬዳዎች ታጅበን ወደፂሆን መጓዝን ለምን እንጠብቃለን? ባርያ ከጌታው ይበልጣል?

ስለዚህ መለመን ያለብን ለወደደው ለመረጠው ህዝቡ ሁሉ የሚያድለውን ሞገስ፣ ማዳን፣ ደስታ፣ በረከትና መጓደጃ የሆነውን የከበረ ርስት ነው።

በአጭር ቃል እራሱን እግዚአብሔርን ነው መሻት ያለብን።

ምናልባት እኛ በቀን አስሬ እየተለዋወጥን የተዘበራረቀ ህይወት ሊኖረን ይችላል...የሚያስፈልገን በእኛ ላይ ስላልተመሰረተ የማይለወጠው ፅኑ የ እግዚአብሔር  ሞገስ/ favor ነው። አስባችሁታል ፍቅሩ ቢዋዥቅ ምን እንደሚውጠን?

የማያባራ አምሮት እንዳለው ሰው አብዝተን ፍቅሩን ከነከፍታ ዝቅታው መሻት አለብን። የበጎነት ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ትሁት ልብ፣ ርህራሄውንና አብሮነቱን አጥብቀን መፈለግ አለብን። ራስህን ስጠኝ፤ አስበኝ ብለን የምንለምንበት ድፍረት ደግሞ አንድ ነው። በበጎ ፈቃዱ የሚሰጠው የእርሱ ሞገስ/ ፀጋ።

እግዚአብሔር ላይ በየሰከንዱ እንደሚያምፅ ሀጥዕ መለመን የምንችለው እንደምህረቱ ብቻ ነው። ሌላማ ምን አለን? በምህረቱ ያስበን። 

Every good thing we have is divine charity. Its undeserved spontaneous favor of God. ልብ ብለን ብንቆጥር ሳንለምነው የቸረን በረከት ይበዛል። ኪዳኑ ራሱ የፀጋ ነው ማለት የማይገባንን በመቀበል የተመረቀ ነው እያልን ነው።

እግዚአብሔር እኛን የዋጀበት ማዳን በእርግጥም ታላቅ ነው። ከዚያ የሚልቅ በረከት አንጠብቅ። ነገር ግን የዚህ በረከት ተካፋይ የሆንን ሁሉ እንደዘማሪው በግል፥ እኔን አስበኝ በማለት መለመን እንችላለን።

ከጌታ ጋር የተሰቀለው ወንበዴም ልመናም ይሄ ነበር።

አስበኝ። የሀጥያቴ ክምር ተደርምሶ እንዳያጠፋኝ ሰግቻለሁና ጌታዬ ሆይ...አስበኝ። በፀጋህ ድረስልኝ። See, its a humble prayer. You're admiting that you are not worth much but a passing thought but "Please! Deal with me not as you would deal with my sinfulness but according to your favor" እያልን ነው።

ብቸኛ ተስፋና መፅናኛችን ይህ ነው። የክርስቶስ ጉብኝት (ብቻ!) ካለብን መንፈሳዊ በሽታዎች ሁሉ ያክመናል። ስለዚህ ቀድመን ስለምህረት ርህራሄው ያወደስነውን አባት፦ ክርስቶስን ካልሰጠኸኝና ካልራራህልኝ ሟች ነኝ ብለን የምንማጠንበት ትሁት ፀሎት ነው።

የእግዚአብሔርን ማዳን ከሩቅ እያዩ በዝማሬ ከማወደስ ባሻገር በግለሰብ ደረጃ እስኪጓደድበት ድረስ የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን የቀረበ ልመና ነው። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ የሚሰራውን ስራ ማወቅ እጅግ መልካም ነገር ነው። ከዚያ መረዳት ተነስተን ደግሞ በዘመናችን ባሉ ስራዎቹ ውስጥ ለመካፈል መለመን እንዳለብን ይህ ፀሎት ያስተምረናል።


2. ያልተበጠሰው የሀጥያት ሰንሰለት (ቁጥር 6–12)

እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤ በደልን፤ ክፉም አደረግን። አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ። እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም። ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት።

ዘማሪው ራሱን በማካተት ራስ ፀደቅነትንና የበላይ መስሎ መታየትን ያስወግዳል። የመጀመርያው ምሳሌ ቀይ ባህር.. እግዚአብሄር ከግብፅ ታድጓቸው ያንጎራጎሩበት አሳዛኝ ታሪክ።

ከግብፅ ከታደጋቸውን አምላክ በላይ የሚፈሩት ግብፅን ነው። እግዚአብሔር በዚህ እያዘነም አድኗቸዋል። ስለስሙ ሲል! ይህ የሚደጋገም theme ነው። ታማኝነቱ የሚመሰረተው በራሱ ማንነት ላይ ብቻ ነው።


3. የምድረበዳው አመፅ (ቁጥር 13–33)፡

የመርሳት አባዜ፡

"ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም።"

Memory is a spiritual discipline! ሆን ብለን ለማስታወስ ካልሞከርን የማይረሳ የተዓምር አይነት የለም። Including our salvation.

የምኞት አባዜ (ቁጥር 14–15)፡

በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው።

እግዚአብሔር የለመንነውን ሁልጊዜ ባይሰጠን እንደሚበጀን ማሳያ ታሪክ ነው። የሚጎዳንን ለመታቀፍ ስንሻና እግዚአብሔር ሲከለክለን እንደበረከት እንድናየውም ያስተምረናል። ፀልየን በተቀበልነው እንዳንጠፋ ምህረቱ ነው የከለለን።

Keller እንደሚለው የኛን shortsighted ልመና እርሱ በሁሉን አዋቂነቱ የሚረዳውን ሁሉ ብናውቅ በምንፀልየው ፀሎት እያረመ ነው የሚመልስልን! መልካምነቱ እዚህ ድረስ ነው!

መሪዎች ላይ የመቅናት መዘዝ(ቁጥር 16–18)፡ በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ።
ቅናት- ሌሎች ያላቸውን ለራስ ከመመኘት ያለፈ አመፅ ነው። እግዚአብሔር የደነገገው ሹመትና ውሳኔ ላይ ጥያቄ ማንሳትም እንደሆነ እንረዳለን።


የጣዖት አምልኮ መዘዝ(ቁጥር 19–23)

በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብፅ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤ እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ። ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር።

የእስራኤል ትልቁ ውድቀት ሳይሆን አይቀርም (ቢያንስ በዚህ ዝርዝር መሰረት) ያዋጣናል ብለው የለወጡት የእግዚአብሔር ክብር ሳር በሚበላ እንስሳ ነው። አባቶች ሀጥያት ደደብ ያደርጋል የሚሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።

Sin makes you stupid because it always exchanges something infinitely valuable for something far smaller. በመካከል ገብቶ የመዳን ምክኒያት የሆናቸው ሙሴ መካከለኛችን የሆነውን ክርስቶስ ያስታውሰናል። ያልጠፋነው በፊቱ ቆሞ ስለሚታይልን ብቻ ነው።


ተስፋን የመናቅ መዘዝ (ቁጥር 24–27)

ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም። በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጕረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም። በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤ ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ።

ከእግዚአብሔር ድምፅ በላይ ሰላዮቻቸውን አመኑ። ፍርሀት ወዲያውኑ ወደአለማመን ሊቀየር ይችላል። ዳዊት በሌላ ቦታ እንደዘመረው "ፍርሃት በሚይዘኝ ጊዜ እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ" እንዳለው ጭንቀታችንን redirect የምናደርግበት ካስፈራን ነገር የሚልቀዝ እግዚአብሔር ካልሆነ ተስፋችንን እስክንንቀው ድረስ እልም ወዳለ አለማመን ያደርሰናል። እምነት የሁኔታችንን አስፈሪነት አያስክደንም። ትኩረታችንን ግን ወደታላቁ አዳኝ እንድናዞር ቀና ያደርገናል። 

የጣዖት አምልኮ መዘዝ( ቁጥር 28–31)

ራሳቸውን ከብዔል ፌጎር ጋር አቈራኙ፤ ለሙታን የተሠዋውን መሥዋዕት በሉ፤ በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ቸነፈርም በላያቸው መጣ። ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ ቸነፈሩም ተገታ፤ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።

እግዚአብሔርን ማምለክ እርግፍ አድርገው ሳይተዉ የደረቡበት ጣዖት አምልኮ እግዚአብሔርን አስቆጣው። ሀጥያት ሲጀማምር እግዚአብሔርን ፈፅመን እንድንክደው በመጋበዝ አይደለም።

ተፎካካሪ መስለው የሚቀርቡትን አማራጭ ጌታ ነኝ ባዮች ያቀርብልናል። ተሸውደን ወጥመዱ ውስጥ ከገባንለት ሳናስበው እግዚአብሔር የሚፀየፈው ቁርኝት ውስጥ ተጠምደን ራሳችንን እናገኛለን።

አሁንም መለስ ብለን ልባችንን ብናይ የተተበተብንበት ብዙ የጣዖት ሰንሰለት አለ። እግዚአብሔርን ብቻ በፍፁም ልብ፣ ነፍስ፣ ሀሳብና ሀይል መውደድ ታላቁ ትዕዛዝ ከሆነ እርሱ ብቻውን ለሁሉም ፍላጎቶቻችን በቂ እንደሆነ ማመን ቢጠበቅብንም እኛ ልባችንን እልፍ ቦታ እየከፋፈልን ለተለያዩ መሻቶቻችን የተቆራኘናቸው ብዙ ጣዖታት አሉ። እንደፊንሃስ ጣልቃ ገብቶ የሚያድነን ፃዲቁ ክርስቶስ ተስፋችን ባይሆን ኖሮ ታላቁን ትዕዛዝ ተላልፈን በሰራነው ታላቅ ሀጥያት መጥፋት ነበረብን።


የማማረር መዘዝ (ቁጥር 32–33)

ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።

የህዝቡ አመፅ ሙሴ ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ እናያለን። መሪነት ቀላል ሆኖ አያውቅም። የተመሪዎቹ ሰዎች ሀጥያት ግን መሪውን ወደሀጥያት ሊመራ አይገባም። This shows us that even Moses who is a symbol of a great leader falls short. He crumbled under the emotional weight. Their sin doesn't excuse his.

ክፉን በክፉ እንዳንመልስ ታዘዘን መሪያችን ክርስቶስ ግን በዚህ ሊወድቅ አይችልም። በዚህ ምድር ላይ የእርሱን ያህል መከራን የተቀበለ ሰው የለም። ግን ደግሞ ሀጥያትን አልሰራም። ስለዚህ የሌሎችን በደል ለራሳችን ድክመት ሰበብ አለማድረግን ከእርሱ እንማራለን።


4. ሙሉበሙሉ ያለመታዘዝ መዘዝ (ቁጥር 34–43)

እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት፣ ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኋላ አሉ፤ እንዲያውም ከሕዝቦቹ ጋር ተደባለቁ፤ ልማዳቸውንም ቀሠሙ፤ጣዖቶቻቸውንም አመለኩ፤ ይህም ወጥመድ ሆነባቸው። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ። የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፣ ለከነዓን ጣዖታት የሠዉአቸውን፣ ንጹሕ ደም አፈሰሱ፤ ምድሪቱም በደም ተበከለች። በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ርስቱንም ተጸየፈ። ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጠላቶቻቸውም በላያቸው ሠለጠኑ። ጠላቶቻቸው ጨቈኗቸው፤ በሥልጣናቸውም ሥር አዋሏቸው። እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤ በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።

ከነዓን መግባት ልባቸውን አልቀየረውም። ጣዖታትን አላወደሙም። ዙርያቸውን ለመምሰል ባዕድ አምልኮን ኮረጁ። ለመምሰል በሞከሯቸው ህዝቦች ተሸንፈው ባርያ ሆኑ። 

Sin always promises freedom. ፍፃሜው ግን ሁልጊዜ ባርነት ነው። እረፍትን ቃል ይገባል። ተቅበዝባዥ ያደርጋል። እግዚአብሔር ታደጋቸው። አመፁ። እግዚአብሔር ቀጣቸው። አለቀሱ። እግዚአብሔር ዳግም ያድናቸዋል እነርሱም ያምፃሉ። ይህ pattern መፅሀፈ መሳፍንት እና የነገስታት ታሪክም ላይ የምናየው አዙሪት ነው። 


5. የእግዚአብሔር ምህረት (ቁጥር 44–46)

ሆኖም ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ፣ ጭንቀታቸውን ተመለከተ፤ ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፤ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ። የማረኳቸው ሁሉ፣ እንዲራሩላቸው አደረገ።

ከዚህ ሁሉሉ የውድቀት ታሪክ በኋላ ይሄን ማንበብ እንዴት ተስፋ ሰጪ ነው! ሆኖም... ባህሪያቸው በስተመጨረሻ በታረመ ጊዜ.. ታማኝነታቸውን prove ባደረጉ ጊዜ አይልም። ህዝቡ የረሳውን ኪዳን እግዚአብሔር አሰበ። እግዚአብሔር እንደአመፃቸው ሳይሆን እንደ ተስፋ ቃሉ ራራላቸው።


6. ምስጋናና ልመና (ቁጥር 47–48)

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ አድነን፤ ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እናቀርብ ዘንድ፣ አንተን በመወደስ እንጓደድ ዘንድ፣ ከሕዝቦች መካከል ሰብስበህ አምጣን። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ ሕዝብም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ታሪክን ማወቅ.. እግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት ያበረታል። ታሪክን መርሳት ወደ አመፅ እንድንንደረደር ይገፈትረናል። አድነን ፥ ሰብስበህ አምጣን በማለት የሚማፀኑት ደግሞ ይገባኛልና ወደነበርኩበት ክብር መልሰኝ ከሚል entitled መንፈስ ሳይሆን የመጨረሻ ግቡ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገንና በውዳሴው ለመጓደድ ነው።

ይሄን ቁርጠኛ አቋም የምናውቀው ፀሎቱን እግዚአብሔርን ከዘላለም እስከዘላለም በመባረክ በማብቃቱ ነው። ዘላለም ውስጥ ምርኮ አለ፣ ነፃነት አለ።

መትረፍረፍ መቸገር፣ መቅበዝበዝ ማረፍ፣ ገናናነት ሀፍረት፣ ታማኝነት አመፅ...የእግዚአብሔር ህዝብ ታሪክ ውስጥ ይሄ ሁሉ መተራመስ ነበረ አለ ይኖራል። በዚህ ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔር ምስጋና ፅኑ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያው ነው። ብሩክነቱ አይለወጥም።

ከዚህ መዝሙር መውሰድ ያለብን ትልቁ ትምህርት እስከመጨረሻው ታማኝ ወደነበረው ክርስቶስ መሮጥን እንጂ "እንደ እስራኤል አትሁኑ" የሚል ሞራላዊ ተግሳፅ ማሳሰብ አይደለም።

Reflection Questions:

ከተዘረዘሩት የእስራኤል አመፃዎች የትኛው ነው ቤተኛ.. የእግዚአብሔርን የቃልኪዳን ታማኝነት መርሳት፣ ቅናት፣ ፍርሃት፣ demanding your own way or compromise? በእኛ ዘመን የምንሰዋላቸው ጣዖታትስ የትኛዎቹ ናቸው? (ምናልባት ተቀባይነት ያላቸው መልካም ነገሮች ይሆናሉ ግን ብቻውን በቂ የሆነውን አምላክ ቦታ እየተጋፉ የሆኑትን ለይተን ወደቦታቸው መመለስ አለብን።)

Report Page